1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፖለቲካ ፓርቲዎች የምርጫ ዝግጅት በደቡብ ክልል

ረቡዕ፣ ጥር 19 2013

አንዳንድ ፓርቲዎችም ለውድድር የመለመሏቸውን እጩዎች ስም ዝርዝርና ፎቶግራፎቻቸውን ከወዲሁ በማህበራዊ የመገናኛ ዘዴዎቻቸው ማስተዋወቅ ጀምረዋል።እንቅስቃሴውን ከጀመሩት መካከል አንዳንዶቹ ልዩ ልዩ  ተግዳሮቶች እንደገጠሟቸው ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/3oUcM
Äthiopien Stadtansicht Awassa
ምስል DW/S. Wegayehu

«መጪው ምርጫ በተስፋም በስጋትም የታጀበ ነው» የፖለቲካ ፓርቲዎች

በኢትዮጲያ የሚገኙ የተለያዩ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመጪው ግንቦት ወር መጨረሻ በሚካሄደው ብሔራዊ ምርጫ የሚሳተፉ አጩ ተወዳዳሪዎችን በመልመል ላይ ናቸው ። አንዳንድ ፓርቲዎችም ለውድድር የመለመሏቸውን እጩዎች ስም ዝርዝርና ፎቶግራፎቻቸውን ከወዲሁ በማህበራዊ የመገናኛ ዘዴዎቻቸው ማስተዋወቅ ጀምረዋል።እንቅስቃሴውን ከጀመሩት መካከል አንዳንዶቹ ልዩ ልዩ  ተግዳሮቶች እንደገጠሟቸው ተናግረዋል።ፖለቲከኞቹ « መጪው ምርጫ በተስፋም በስጋትም የታጀበ ነው» ሲሉ ለዶቼ ቬለ (DW) አስተያየታቸውን አጋርተዋል። 
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ኂሩት መለሰ
አዜብ ታደሰ