1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፖለቲካ ፓርቲዎች ስለቀጣዩ ምርጫ ምን ይላሉ?

ረቡዕ፣ ኅዳር 23 2013

ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አሕመድ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በተገኘበት ቀጣዩን ምርጫ አስመልክቶ ከፖለቲካ ፓርቲዎች አመራር እና ከሲቪክ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት  ማድረጋቸውን የጠቅላይ ሚንሥትር ጽሕፈት ቤት ጠቅሷል። ፖለቲካ አመራር አባላቱ ስለ ውይይት መድረኩ አስተያየታቸው ምን ይመስላል?

https://p.dw.com/p/3m8Gg
Äthiopien Logo Prime Minister Office

የምርጫ ቦርድ በተገኘበት ስለቀጣዩ ምርጫ ውይይት ተካኺዷል

ጠቅላይ ሚንሥትር ዐቢይ አሕመድ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ በተገኘበት ቀጣዩን ምርጫ አስመልክቶ ከፖለቲካ ፓርቲዎች አመራር እና ከሲቪክ ማኅበረሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት  ማድረጋቸውን የጠቅላይ ሚንሥትር ጽሕፈት ቤት ጠቅሷል። የውይይቱ ተሳታፊዎች ምቹ ኹኔታ እንዲፈጠር፤ የሕግ የበላይነት እንዲከበር፤ የሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች ተሳታፊነት እንዲረጋገጥ የሚሉ አስተያየቶች መሰጠታቸውን እና በርካታ ጉዳዮችን ማንሳታቸውንም ጽ7ቤቱ ዘርዝሯል። የውይይቱ ተሳታፊዎች የፖለቲካ አመራር ከዶይቸ ቬለ (DW)ጋር በነበራቸው ቃለ መጠይቅ ሲናገሩ ከጠቅላይ ሚንስትሩ ጋር የነበረው ውይይት፦ «በጣም ጠቃሚ ነበር» ያሉ ይገኙበታል። በሌላ በኩል ደግሞ፦ ምክክሩ «የጦርነት ጭንቀት መንፈስን ለመግፈፍ» የተሞከረ እንደኾነ የሚገልጥ አስተያየትም ተሰጥቷል። የፖለቲካ አመራር አባላቱ ስለ ውይይት መድረኩ አስተያየታቸውን እንዲያካፍሉ በመጠየቅ የአዲስ አበባው ወኪላችን ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር ቀጣዩን ዘገባ አጠናቅሯል። 
ዮሐንስ ገ/እግዚአብሔር 
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ነጋሽ መሐመድ