1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፖለቲካ ተንታኝ አስተያየትና ወይይት

እሑድ፣ ሰኔ 16 2011

የእስከ ትናንቱ ፈተና አልበቃ ያለ ይመስል ትናንት መንግሥት፣ «መፈንቅለ መንግስት» ባለዉ ሴራ ባሕር ዳር ላይ የአማራ ክልል መሪዎች መገደል-መቁሰላቸዉ፣ አዲስ አበባ ደግሞ የሐገሪቱ የጦር ኃይል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹምና ሌላ ጄኔራል መገደላቸዉ አሳሳቢዉን ሒደት አስጊ አድርጎታል

https://p.dw.com/p/3Kxe0
Abiy Ahmed Äthiopien
ምስል picture-alliance/AP Photo

የግድያ፣ መፈንቅለ መንግስቱ ሴራ ምክንያትና ዉጤቱ

 ኢትዮጵያ አምና መጋቢት የጀመረችዉ ፖለቲካዊ ለዉጥ አብዛኛዉን የሐገሪቱን ሕዝብ ያስደሰተ፣በአብዛኛዉ ሕዝብ የተደገፈ ነዉ።ለዉጡ ለአፍሪቃ አብነት፣ለዓለም ሰላምና ዴሞክራሲ ተስፋ ሰጪነቱን የዉስጥም የዉጪም ታዛቢዎች መስክረዉለታል።ይሁንና የለዉጡ ጅምር ጉዞ በጎሳ ግጭት፣በግድያ፣በስርዓተ አልበኝነት፣ በዉዝግብና እሰጥ አገባ መታጀቡ ብዙዎችን እንዳሳሰበ ዓመት አልፎ ሰወስተኛ ወሩ ተጋመሰ።የእስከ ትናንቱ ፈተና አልበቃ ያለ ይመስል ትናንት መንግሥት፣ «መፈንቅለ መንግስት» ባለዉ ሴራ ባሕር ዳር ላይ የአማራ ክልል መሪዎች መገደል-መቁሰላቸዉ፣ አዲስ አበባ ደግሞ የሐገሪቱ የጦር ኃይል ጠቅላይ ኤታማዦር ሹምና ሌላ ጄኔራል መገደላቸዉ አሳሳቢዉን ሒደት አስጊ አድርጎታል።የታዛቢዎችን ጥያቄም አጭሯል። የምስራቅ አፍሪቃ የፖለቲካ ተንታኝ ዶክተር ሙከረም ሚስባሕን አነጋግረናል።

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ