1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የፌደራል አቃቤ ሕግ እና የIOM ውይይት

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 23 2012

ከውጭ ወደ ሀገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያውያን ፍልሰኞችን መልሶ ለማቋቋም ድጋፍ ተጠየቀ።  ኢትዮጵያ ከ ሦስት ሚሊዮን  በላይ ዜጎቿ  በውጭ ሀገር ፈልሰው  የሚኖሩ እና አንድ ሚሊዮን ገደማ የውጭ  ፍልሰተኞችን  ተቀብላ የምታስተናግድ ሀገር ብትሆንም እስካሁን የፍልሰተኞች አስተዳደር ፖሊሲ የላትም።

https://p.dw.com/p/3Vbyo
Äthiopien Stadtansicht Mekele
ምስል DW/M. Hailessilasie

«ሕገ ወጥስደት እና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ»

ከውጭ ወደ ሀገራቸው የሚመለሱ ኢትዮጵያውያን ፍልሰኞችን መልሶ ለማቋቋም ድጋፍ ተጠየቀ። ኢትዮጵያዊያን በሦስት አቅጣጫዎች ከሀገራቸው በሕገወጥ መንገድ የሚወጡ ሲሆን  አብዛኞቹ  ተመላሾች ከአረብ ሃገራት የሚመጡ መሆናቸውን የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ አስታውቋል። ኢትዮጵያ ከ ሦስት ሚሊዮን  በላይ ዜጎቿ  በውጭ ሀገር ፈልሰው  የሚኖሩ እና አንድ ሚሊዮን ገደማ የውጭ  ፍልሰተኞችን  ተቀብላ የምታስተናግድ ሀገር ብትሆንም እስካሁን የፍልሰተኞች አስተዳደር ፖሊሲ የላትም። ሰለሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ ተከታዩን ልኮልናል።

ሰለሞን ሙጬ

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ