የፀረ ሽብር ሕግ
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 14 2011ማስታወቂያ
«አፋኝ» ተብሎ የሚወቀሰዉን የኢትዮጵያ የፀረ-ሽብር ሕግን ጠቅሶ ተጠርጣሪዎችን ማሰርና መክሰስ የፍትሕ ስርዓቱን ለማሻሻል የሚደረገዉን ጥረት የሕዝብ አመኔታ ሊያሳጣዉ እንደሚችል አንዲት የሕግ ባለሙያና ሌላ ጋዘጠኛ መከሩ።የሕግ ባለሙያና ጠበቃ አዲስ መሐመድ እንደሚሉት ተጠርጣሪዎችን «ይሻሻላል» የተባለዉን ፀረ-ሽብር ሕግን ጠቅሶ መክሰስ ተስፋ የተጣለበትን ለዉጥም ሊያደናቅፈዉ ይችላል።ግዮን የተባለዉ መፅሔት ዋና አዘጋጅ ሮቤል ምትኩ በበኩሉ ጋዜጠኞችንና ፖለቲከኞችን በፀረ-ሽብር ሕጉ መክሰስ «ስሕተት ነዉ» ይላል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ