1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጥምቀት በዓል በጃንሜዳ

ማክሰኞ፣ ጥር 11 2013

የ2013 ዓ.ም የጥምቀት በዓል በአዲስ አበባ ደመቅ ባለ ድባብ ተከበረ። በበዓሉ በተለይም በጃን ሜዳ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝበ ክርስትያን የታደመ ሲሆን ለበዓሉ የተዘጋጁ ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ክዋኔዎች ባማረ ሁኔታ ተከናውነዋል።

https://p.dw.com/p/3o8Xp
Äthiopien Ketera Timket Fest
ምስል Yohannes G/Egziabher/DW

ደመቅ ባለ ድባብ ተከበረ

የ2013 ዓ.ም የጥምቀት በዓል በአዲስ አበባ ደመቅ ባለ ድባብ ተከበረ። በበዓሉ በተለይም በጃን ሜዳ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሕዝበ ክርስትያን የታደመ ሲሆን ለበዓሉ የተዘጋጁ ልዩ ልዩ መንፈሳዊ ክዋኔዎች ባማረ ሁኔታ ተከናውነዋል። የባህልና ቱሪዝም ሚኒስትር ዶክተር ኂሩት ካሣው በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የማይዳሰስ ቅርስ ሆኖ የተመዘገበውን የጥምቀት በዓል ልዩ ጥበቃና እንክብካቤ ልናደርግለት ይገባል ብለዋል። ለምዕመኑ መልዕክትና ቡራኬ ያስተላለፉት ብፁዕ አቡነ ማትያስ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስትያን ፖትርያርክ ጥምቀት ከዚህ በላቀ ደረጃ እንዲከበር ሁሉም የሚችለውን እንዲያደርግ ጠይቀዋል። በበዓሉ አከባበር ላይ እድምተኛው ሕዝብ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ቢያደርግም መሰባሰቡና እጅግ መጠጋጋቱ የኮሮና ተኅዋሲ መከላከል መርህን የተከተለ እንዳልነበር ለመታዘብ ችለናል።  


ሰለሞን ሙጬ

 
ማንተጋፍቶት ስለሺ
ሸዋዬ ለገሠ