1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

«የጥላቻ እና የፍቅር ቃላት» ድራማ፥ ክፍል 8

እሑድ፣ ሐምሌ 12 2012

ይኽ  ወንጀል ተፋላሚዎቹ በሚል ዐቢይ ርእስ የሚቀርብላችሁ ተከታታይ የራዲዮ ድራማ ነው።

https://p.dw.com/p/3fYHA
DW Crime Fighters Serienmotiv „Our tongue, our land“

«የጥላቻ እና የፍቅር ቃላት»

የጥላቻ እና የፍቅር ቃላት በሚል ዐቢይ ርእስ የቀረበው ድራማ ስምንተኛ ክፍል ጀምሯል። ይኸ የራዲዮ ድራማ በማጋንጌ ጎሳዎች መካከል ባለው ትንቅንቅ እና በአገሪቱ በተንሰራፋው የጥላቻ ንግግር ላይ ያተኩራል። ባለፈው ሳምንት ጥንዶቹ ጁን እና ዊላ የቲሪቤ ጦረኞች በዴሬምባዎች ላይ ያቀዱትን ጥቃት ለማስቆም በጋራ ጥረት ጀምረዋል። ዋና ኢንስፔክተር ኦፓንዴ የማለለለፓ ሊቀ-መንበር ዱምባ ለሟቿ ባንኩ ያላቸውን ጥልቅ ፍቅር ሲረዱ ከእስር ለቀዋቸዋል። አሁን ዋና ኢንስስፔክተር ኦፓንዴ ከሥራ ባልደረባቸው ኢንስፔክተር ኒምሮድ ጋር በቢሯቸው በጉዳዩ ላይ እየመከሩ ነው። «ወደ ፍትኅ የሚወስደው አስቸጋሪ መንገድ» የተሰኘው ስምንተኛ ክፍል ተጀመረ።  


ደራሲ፦ ክሪስፒን ምዋኪዱ
አዘጋጅ፦ ማንተጋፍቶት ስለሺ