1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጤፍ ባለቤትነት ውዝግብ መፍትሔ ሊያገኝ ይሆን?

ማክሰኞ፣ ጥር 19 2012

አንሼይንት ግሬይን ለተባለ የኔዘርላንድስ ኩባንያ የተሰጠውና ኢትዮጵያን ያስቆጣው የጤፍ የባለቤትነት መብት ውዝግብ መፍትሔ ሊያገኝ የተቃረበ ይመስላል። ይኸ ጉዳይ መፍትሔ ሊያገኝ ቢቃረብም ጤፍን መሰል አዝርዕትና ልዩ ልዩ እጽዋት ግን በማይገባቸው ኩባንያዎች ስም ተመዝግበው ይገኛሉ።

https://p.dw.com/p/3WwAc
Bildergalerie Äthiopien Teff
ምስል DW/J. Jeffrey

ጤፍን መሰል አዝርዕትና እጽዋት በማይገባቸው ኩባንያዎች ስም ተመዝግበው ይገኛሉ

አንሼይንት ግሬይን ለተባለ የኔዘርላንድስ ኩባንያ የተሰጠው እና ኢትዮጵያን ያስቆጣው የጤፍ የባለቤትነት መብት ውዝግብ መፍትሔ ሊያገኝ የተቃረበ ይመስላል። በተወሰኑ የአውሮፓ አገሮች ዛሬም ድረስ ከጤፍ የተዘጋጀ ዱቄት አሊያም ማናቸውም የምግብ ዓይነት ለሽያጭ ሲቀርብ ለዚሁ ኩባንያ የተወሰነ ክፍያ ይደርሰዋል። 
ስሙን ሔልዝ ኤንድ ፕርፎርማንስ ኢንተርናሽናል (HPFI) ወደሚል የቀየረው የኔዘርላንድስ ኩባንያ የጤፍ አዘገጃጀት ሒደት የባለቤትነት መብት ባለቤት ሆኖ በአውሮፓ የተመዘገበው በጎርጎሮሳዊው 2007 ዓ. ም. ነበር።

ይኸ ኢትዮጵያውያንን ያስቆጣ የባለቤትነት ጉዳይ መፍትሔ ሊያገኝ ቢቃረብም ጤፍን መሰል አዝርዕት እና ልዩ ልዩ እጽዋት ግን በማይገባቸው ኩባንያዎች ስም ተመዝግበው ይገኛሉ። የዛሬዉ ጤናና አካባቢ በጤፍ ባለቤትነት ላይ የጠናከረ ዝግጅት አለዉ።ያን ፊሊፕ ያጠናቀረዉን የበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለ ያቀርበዋል።

ሙሉ ዘገባውን ለማድመጥ የድምፅ ማዕቀፉን ይጫኑ።


ያን ፊሊፕ ቪልሔልም/ ይልማ ኃይለሚካኤል