1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጤና ባለሙያዎችና የህክምና ቁሳቁስ እጥረት የባሕር ዳር

ማክሰኞ፣ ሰኔ 8 2013

በባሕር ዳር ከተማ ከሚገኙ ጤና ጣቢያዎች መካከል አንዱ የሆነው ሀን ጤና ጣቢያ ከፍተኛ የቦታ፣ የቤተሙከራ ቁሳቁስና የባለሙያ እጥረት እንዳለበት የጤና ጣቢያው ሠራተኞች ይገልፃሉ።

https://p.dw.com/p/3uyXu
Äthiopien Mengist Kebede, Chirurg und Gynäkologe im Han-Gesundheitszentrum in Bahir Dar
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

ለችግሩ ማሳያ የሀና ጤና ጣቢያ

በባሕር ዳር ከተማ ከሚገኙ ጤና ጣቢያዎች መካከል አንዱ የሆነው ሀን ጤና ጣቢያ ከፍተኛ የቦታ፣ የቤተሙከራ ቁሳቁስና የባለሙያ እጥረት እንዳለበት የጤና ጣቢያው ሠራተኞች ይገልፃሉ። በጤና ጣቢያው የቀዶ ጥገናና የማህፀንና ጽንስ ህክምና ባለሙያ አቶ መንግሥት ከበደ ለዶይቼ ቬለ እንደተናገሩት ባሉ ችግሮች ምክንያት ተገልጋዮችን ባግባቡ መርዳት አልተቻለም። የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር ጤና መምሪያ ኃላፊ አቶ አስማማው ሞገስ የቦታ እጥረት ችግርን ለመፍታት እየተሠራ እንደሆነ፣ የባለሙያ ቅጥር ለማካሄድም በጀት መመደቡንና ከክልሉ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ጋር እየተነጋገርንበት ነው ይላሉ። የቤተሙከራ ቁሳቁሶችን በተመለከተም በሂደት የሚፈቱ እንደሚሆኑ ነው የተናገሩት።

ወላዶችን በተገቢው መንገድ ለማስተናገድ የባለሙያ፣ የቦታ ጥበትና እንዲሁም የህክምና ግብዓቶች እንዳሉባቸው አንዳንድ በባሕር ዳር ከተማ የሚገኙ ጤና ጣቢያ ባለሙያዎች ቅሬታ ያቀርባሉ። ባለሥልጣናቱ ደግሞ ለአንዳንዶቹ መፍትሔ እየተፈለገ እንደሆነ ሲናገሩ፣ አንዳንድ ችግሮችን ደግሞ አንዱ ወደ ሌላው ሲገፋቸው እንደሚታይ  ነው የሚጠቀሰቀው፣ ተገልጋይ እናቶችም በተለይ የክፍልና የመገልገያ ቁሳቁሶች እጥረት አጋጥሞናል ብለዋል፡፡

Äthiopien Mengist Kebede, Chirurg und Gynäkologe im Han-Gesundheitszentrum in Bahir Dar
ምስል Alemnew Mekonnen/DW

 የሀን ጤና ጣቢያ ባለሙያዎች በተለይ ወላዶችን ለማስተናገድ የክፍል እጥረትና በቂ ባለሙያ አለመኖር ፈተና እንደሆነባቸው ነው ያመለከቱተ። የአገልግሎት ፈላጊ እናቶች ከቀን ቀን እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ የባለሙያ፣ የህክምና ቁሳቁሶች እጥረትና የቦታ ጥበት ከፍተኛ ጫና እየፈጠረባቸው እንደሆነ ለዶቼ ቬለ አስረድተዋል፡፡

በሀን ጤና ጣቢያ የቀዶ ህክምና ከተደረገላቸው እናቶች መካከል የወ/ሮ አዝመራ አበዛውና የወ/ሮ ሙሉዬ ቢክስ በሰጡት አስተያት ባለሙያዎቹ ነብስ ለማዳን የሚያደርጉት ጥረት የሚመሰገን መሆኑን ጠቁመው የኦፕሬሽንና የማዋለጃ ክፍሎች ጥበት ግን በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ ባለው የክፍል ጥበት ምክንትም እስከ 4 እናቶች በጋራ ህክምና ስለሚወስዱ የግል ሚስጢራቸውን ለግላቸው ማድረግ አልቻሉም፡፡

ዓለምነው መኮንን

ሸዋዬ ለገሠ