1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጣልያን የምርጫ ውጤት በአውሮፓ ሕብረት ያለው አንድምታ

ማክሰኞ፣ መስከረም 17 2015

አዲሱ የሚመሰረተው የጣልያን መንግስት አጣማሪ ፓርቲዎች ቅድሚያ ለአገር ውስጥ ጉዳዮች የሚሰጥ፣ በስደተኞች ላይም ጠንከር ያለ አቋም የሚያራምድ በተለይም ደግሞ የአውሮፓ ሕብረት የሚወስዳቸውን አቋሞችን የሚቃወም ጥምረት መሆኑ ይታወቃል። ይህ ለሕብረቱ ፈተና ሊሆንበት እንደሚችል ይገመታል።

https://p.dw.com/p/4HPLs
Wahl in Italien | Wahlabend in der FdI Parteizentrale
ምስል Guglielmo Mangiapane/REUTERS

አውሮፓና ጀርመን

ጤና ይስጥልን ውድ የአውሮፓና ጀርመን ፕሮግራም ተከታታዮች። በዛሬው ዝግጅታችን በጣልያን ባለፈው እሁድ በተካሄደው ምርጫ የቀኝ ወግ አጥባቂ ፓርቲዎች ጥምረት ማሸነፉ ይታወቃል። አገሪቱም ለመጀመሪያ ጊዜ ሴት ጠቅላይ ሚኒስቴር ሊኖራት ነው። የጣልያን ምርጫ ውጤት ለአውሮፓ ሕብረት ያለው አንደምታና የጣልያን ነዋሪዎች አስተያየት ያካተተ ዝግጅት ይዘን ቀርበናል መልካም ቆይታ።

የጣልያን ወንድማማቾች ፓርቲ መሪ ጆርጂያ ሜሎኒ እሳቸው የጠቅላይ ሚኒስትርነቱን ቦታ የሚያስጨብቻቸውን የሶስት የቀኝ  ወግ አጥባቂ ፓርቲዎች ጥምረት ማሸነፉን ተከትሎ  ለደጋፊዎቻቸው ባሰሙት ንግግር ``ከነገ ጀምሮ እሴቶቻችን ማሳየት አለብን፣ ጣልያናውያን መርጣችሁናል እናም እሴቶቻችንን አንክድም።`` በማለት ገልጸዋል።
ስለአጠቃለዩ የምርጭው ሁኔታ የብራስልሱ ወኪላችንን ገበያው ንጉሴን አሁን ሸነፉት የ3 ፓርቲዎች ጥምረት ከሁለተኛው የዓለም ጦርነት bw,ዲህ ፖለቲካውን ወደ ቀኝ ወግ አጥባቂ ለውጥ ያደረገበት እንደሆነ ገልጾልናል።
የቀኝ ወግ አጥባቂ ፓርቲዎች ጥምረት ማሸነፉን ተከትሎ በተለያዩ የጣልያን ግዛቶች የሚኖሩ መራጮች የተለያየ አስተያየት ሰንዝሯል። የሮማ ከተማ ነዋሪ ዳንኤላ ፎርኒ

"እናያለን! የኢጣልያ ወንድማማቾች ፓርቲ መሪ ጂርጂያ ሜሎኒ ሁሉንም ጣልያናውያንን መወከል  እንደምትችል ማረጋገጥ አለባት። በተለይም  ለቀኝ ክንፍ ፓርቲዎችን ድምፅ የሰጡትን  ጣልያኖች ሁሉ እንደምትወክል ማረጋገጥ አለባት ። ከተሳካላት ደግሞ መሪ ሆና ትቀመጣለች ፤ አለዚያ ግን ለሐዘን ትዳረጋለች ። "

Wahl in Italien | Wahlabend in der FdI Parteizentrale
ምስል Gregorio Borgia/AP/picture alliance

 ሌላው የሮም ከተማ ነዋሪ   የሆነው ጂአንሉይ ፒርኔሺ እንዲህ ይላል: -
"በአጠቃላይ  እኛ  ጣሊያኖች ሁሌም እምነት አለን ። ነገር ግን ይህ የፍልስፍና ፅንሰ ሀሳብ ነው። ምክንያቱም በህይወት እምነት ከሌለህ   ወደፊት መራመድ አትችልም ። ሁላችንም ከዚህ ጊዜ አንስቶ ፣ ባለፉት 30፣ 35 ወይም 40 ዓመታት ውስጥ ለአሥርት ዓመታት  ያህል በእኛ ላይ በሚመሩት ሰዎች ምርጫ ላይ እውነተኛ እምነት ሊኖረን እንደሚችል ተስፋ እናደርጋለን ። "
ፋብዮላ የተባለች ጣልያናዊትም በምርጫው ተሳትፋለች እሷ የአሸናፊዋ የጆርጅያ ሜሎኒ አድናቂም ደጋፊም አደለችም።
"እውነቱን ለመናገር የሷ ተከታይ አደለሁም፣ የሷ ፓርቲ አባል የሆነበት ጥምረትን ግን ወድጀዋለሁ። ።"አንድርዮ ሪዞኒ ሌላው ድምጽ ከሰጡት ጣላያናውያን መካከል ነው። እሱ በግሉ አሸናፊዋ ወይዘሮ ጆርጅያ ሜሎኒን አይወዳቸውም። ጣልያናውያን ግን እንደሳቸው አይነት ሰዎች ይወዳሉ ብልህ አይደሉም ሲል በምሬት ተናግሯል። 
``እኔ በግሌ አልወዳትም ። ነገር ግን ለኢጣሊያኖች የምታስፈልጋቸው እሷ ናት ። ጣልያናውያን ብልህ አይደሉም።  እኔ ለየት ያለ ሐሳብ አለኝ።  ጣሊያውያን ወደ ታች ወረድ ብለው ማሰብ አለባቸው። ወረድ ብለው ባሰቡ ቁጥር   ከእንቅልፋቸው ነቅተው አንድ ነገር እንዲለውጡ ያስችላቸዋል።  "

Wahl in Italien | Giorgia Meloni in einem Wahllokal in Rom
ምስል Massimo Percossi/ANSA/picture alliance

በምርጫው ውጤት ደስተኛ አይደለሁም ግን ምን ይደረግ ዴሞክራሲ ነው የሚል ቅሬታ አዘል አስተያየት የሰጠች ጣልያናዊት አስተያየት እናስከትል
"ደስተኛ አደለሁም። እናም ድምጼን ለሷ አልሰጠሁም። ይሁን እንጂ ዲሞክራሲ ነው"።

ፍራንቼስኮ ሎሎቢሪዳ ፤ በጣልያን የተወካዮች ምክርቤት  የወንድሞች ፓርቲ አባላት  ቡድን መሪ ናቸው። እሳቸው የሰጡትን አስተያየት እናስደምጣችሁ።
" ሜሎኒ የጣልያንና የአውሮፓ ወግ አጥባቂዎች መሪ ናት ። እርሷም እንደ ሁሉም ሴቶች ከኛም የበለጠ  ወደፊት ለሚመጡት ነገሮች ኃላፊነት ይሰማታል ። በጣሊያን ወንድሞችና በጥምረቱ ባገኘችው ውጤት በጣም ረክታለች ። ከሁሉም በላይ ግን የገባችውን ቃል ለመጠበቅ ለራሷ ሕዝብ መሥራት እንዳለባት ተገንዝባለች ። ጣሊያን በዓለም አቀፍ ደረጃ ጥቅሟን ለማስከበር ስትጥር ቆይታለች። በእኛ አመለካከት ደግሞ ከአጋሮቿ ጋር ታማኝና ልባዊ ግንኙነት ቢኖራትም የራሷን ሕዝብ ጥቅም ማስጠበቅ ትችላለች ።
በፍርሃት እንዋጣለን የሚል ስሜት የለኝም። ባለፈው ሳምንት በጣሊያን ከፈረንሳይ አምባሳደር ጋር ተወያይቻለሁ ። አውሮፓን ወይም ሌሎች ቅድሚያ የሚሰጧቸውን ጉዳዮች በተመለከተ በተለይም በሜድትራንያን አካባቢ ብዙ የሚያመሳስሉን ጭብጦች አሉን ። በተጨማሪም የተረጋጋ ሰላም በማስፈኑ ረገድ ትልቅ እዳ ያለን አገራት በመሆናችን በአውሮፓ የትብብር ማዕቀፍ ውስጥ አብረን መስራት አለብን ። አውሮፓ ቁልፍ ነጥብ እንደሆነች በማሰብ ከሌሎች የአውሮፓ አገሮች ጋር መሥራትም አለብን ። ይሁን እንጂ የሕዝቡ ፍላጎት በመረጧቸው መንግስታት መረጋገጥ አለበት። "አዲሱ የሚመሰረተው የጣልያን መንግስት አጣማሪ ፓርቲዎች ቅድሚያ ለአገር ውስጥ ጉዳዮች የሚሰጥ፣ በስደተኞች ላይም ጠንከር ያለ አቋም የሚያራምድ በተለይም ደግሞ የአውሮፓ ሕብረት የሚወስዳቸውን አቋሞችን የሚቃወም ጥምረት መሆኑ ይታወቃል። ይህ ለሕብረቱ ፈተና ሊሆንበት እንደሚችል ወኪላችን ገበያው ንጉሴን በሰጠን ገለጻ አስረድቷል።
በጣልያን ምርጫ ውጤት ላይና አንደምታው ላይ ተንተርሰን ያዘጋጀነውን በዚሁ ፈጸምን ከዝግጅቱ ጋ

Wahl in Italien | Wahlabend in der FdI Parteizentrale
ምስል Guglielmo Mangiapane/REUTERS
Wahl in Italien | Wahllokal in Rom
ምስል Alessandra Tarantino/AP/picture alliance

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር 

ታምራት ዲንሳ