1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት መግለጫ

ማክሰኞ፣ ነሐሴ 4 2013

የጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት የመከላከያ ሠራዊቱ፣ የክልል ልዩ ኃይሎችና ሚሊሻዎች፣ «ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የተነሣ የክህደት ኃይልና የውጭ እጆች ስውር ደባ ለመደምሰስ» እንዲነሱ አቅጣጫ ማስቀመጡን ዐስታወቀ። ጽሕፈት ቤቱ፦ «ሀገርን የመከላከል ዘመቻ» ባለው መግለጫ ዕድሜያቸው የሚፈቅድላቸው ኢትዮጵያውያን ጦሩን እንዲቀላቀሉም ጥሪ አቅርቧል።

https://p.dw.com/p/3yoZ6
Äthiopien Logo Prime Minister Office

ቃለ መጠይቅ የጠቅላይ ሚንሥትር ጽሕፈት ቤት መግለጫ

የጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት የመከላከያ ሠራዊቱ ፣ የክልል ልዩ ኃይሎችና ሚሊሻዎች፣ «ኢትዮጵያን ለማፈራረስ የተነሣ የክህደት ኃይልና የውጭ እጆች ስውር ደባ ለመደምሰስ» እንዲነሱ አቅጣጫ ማስቀመጡን ዐስታወቀ። ጽሕፈት ቤቱ ዛሬ ባወጣው ፤ «ሀገርን የመከላከል ዘመቻ» ባለው መግለጫ ዕድሜያቸው የሚፈቅድላቸው ኢትዮጵያውያን ጦሩን እንዲቀላቀሉም ጥሪ አቅርቧል። ጽሕፈት ቤቱ «ጁንታው» ያለው ኃይል የከፈተ ጥቃት ሕዝባዊ መልክ እንዲይዝ በማድረጉ ያንኑ ለመመከት ሕዝባዊ ምላሽ እንደሚያሻውም ነው የገለጸው። አያይዞም  «ውጊያው የትግራይን ሕዝብ ምሽግ ካደረገው እኩይ ኃይል ጋር እንጂ ከትግራይ ጋር» እንዳልሆነ በማመልከትም «መጠቀሚያ የሆነውን የትግራይ ሕዝብ ብሎም መላዋ ኢትዮጵያን ከአሸባሪው ቡድን ነጻ ለማውጣትና የሀገራችንን ሰላምና አንድነት ለማስከበር ነው» ሲልም በመግለጫው ዘርዝሯል። የኢትዮጵያ መንግሥት በትግራይ ክልል ሲደረግ የነበረውን ሕግ ማስከበር ያለውን ውግያ የተናጥል የተኩስ አቁም አድርጎ ከትግራይ መውጣቱን ባለፈው ሰኔ ወር አስታውቆ ነበር። የትግራይ አማጽያን ግን በወቅቱ የመንግሥትን የተናጥል የተኩስ አቁም አልተቀበሉትም። በቅድመ ሁኔታ ላይ የተመሰረተ የተኩስ አቁም ማድረግ እንደሚፈልጉ በመግለጽም ውጊያው ወደ አጎራባች የአማራ እና አፋር ክልሎች ተስፋፍቶ ለብዙዎች ሞት፣ የአካል ጉዳት እና በሺዎች ለሚቆጠሩ ዜጎች የመፈናቀል ምክንያት መሆኑ እየተነገረ ነው።

ሰለሞን ሙጬ

ማንተጋፍቶት ስለሺ