1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠቅላይ ሚኒስትሩ የደቡብ ክልል ጉብኝት

ረቡዕ፣ የካቲት 18 2012

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ዛሬ በደቡብ ክልል የከምባታ ጠምባሮ እና የሀላባ ዞኖችን ሲጎበኙ ውለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው በየስታዲየሞቹ ለተሰበሰቡ ነዋሪዎች ንግግር አሰምተዋል ፣ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋርም ተወያይተዋል ።

https://p.dw.com/p/3YT8T
Friedensnobelpreis 2019 Äthiopien | Ministerpräsident Abiy Ahmed
ምስል picture-alliance/dpa/B. Pedersen

ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር ተወያይተዋል

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ዛሬ በደቡብ ክልል የከምባታ ጠምባሮ እና የሀላባ ዞኖችን ሲጎበኙ ውለዋል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው በየስታዲየሞቹ ለተሰበሰቡ ነዋሪዎች ንግግር አሰምተዋል ፣ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋርም ተወያይተዋል ። ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ሙሁራን ጠቅላይ ሚኒስትሩ የደቡብ ክልል የሚያደረጉትን ተከታታይ ጉበኝት አንድም የምርጫ ዝግጅት አሊያም የመበታተን አደጋ ያንዣበበትን የደቡብ ክልል ለመታደግ ያለመ ሊሆን ይችላል የሚሉ አስተያየቶችን እየሰነዘሩ ይገኛሉ።

 

ሸዋንግዛው ወጋየሁ

አዜብ ታደሰ

ነጋሽ መሐመድ