1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጠ/ሚ ዐብይ ሕዝባዊ መድረክ ቅድመ-ዝግጅት በፍራንክፈርት

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 20 2011

በአስር ሺዎች የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን እና ውልደ ኢትዮጵያውያን በነገው ዕለት ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ጋር በፍራንክፈርት ከተማ በሚካሄደው ሕዝባዊ ውይይት ላይ ለመካፈል ጀርመን መግባት መጀመራቸውን የመርሃ ግብሩ አስተባባሪዎች ገለጹ::

https://p.dw.com/p/37P4E
Abiy Ahmed in Frankfurt  Commerzbank Arena Stadion
ምስል DW/E. Fekade

«አንድ ሆነን እንነሳ ነገንም እንገንባ»

 " አንድ ሆነን እንነሳ ነገንም እንገንባ " በሚለው የለውጡ ኃይል መሪ ቃል በተዘጋጀው በዚሁ አውሮፓ አቀፍ ታሪካዊ ጉባኤ ኢትዮጵያውያን ዝግጅቱ ለሚከናወንበት ትልቁ የኮሜርዝ ባንክ አሬና ስታዲየም ኪራይ እና የተለያዩ ወጪዎችን ለመሸፈን የተሳካ የገቢ ማሰባሰቢያ መርሃግብር ማካሄዳቸውንም በፍራንክፈርት የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጄኔራል ቆንሱል አቶ ምህረተዓብ ሙሉጌታ ለ DW ገልጸዋል:: በጀርመን ነዋሪ የሆኑ ከ 200 በላይ ወጣቶች ዝግጅቱን በበጎ አገልግሎት ለማስተባበር በፈቃደኝነት የተመዘገቡ ሲሆን ከመላው አውሮፓ በመኪና ለሚመጡ ታዳሚዎችም ከ 10 ሺህ በላይ የመኪና ማቆሚያ ስፍራዎች መዘጋጀታቸው ታውቋል ። ዝርዝሩን እንዳልካቸው ፈቃደ አጠናቅሮታል::

እንዳልካቸው ፈቃደ

አዜብ ታደሰ