1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የግሩም መዝሙር እና አልሑሴኒ አኒቮላ ሙዚቃ በድሬዳዋ

እሑድ፣ መጋቢት 8 2011

ኢትዮጵያዊው ግሩም መዝሙር እና የኒጀሩ አልሑሴኒ አኒቮላ ባለፈው ሳምንት በድሬዳዋ አሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴ መድረክ የሙዚቃ ሥራዎቻቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ የሙዚቃ ድግስ ሁለቱ ባለሙያዎች በጥምረት የጀመሩት ፓን አፍሪካን ፔንታቶኒክ ፕሮጀክት አንድ አካል ነው። 

https://p.dw.com/p/3FDco
Konzert in Dira Dawa, Äthiopien
ምስል DW/M. Teklu

የግሩም መዝሙር እና አልሑሴኒ አኒቮላ ሙዚቃ በድሬዳዋ

ኢትዮጵያዊው ግሩም መዝሙር እና የኒጀሩ አልሑሴኒ አኒቮላ ባለፈው ሳምንት በድሬዳዋ አሊያንስ ኢትዮ ፍራንሴ መድረክ የሙዚቃ ሥራዎቻቸውን አቅርበዋል። የድሬዳዋ የሙዚቃ ድግስ ሁለቱ ባለሙያዎች በጥምረት የጀመሩት ፓን አፍሪካን ፔንታቶኒክ ፕሮጀክት አንድ አካል ነው። 

"የኒጀር ሙዚቃ እና የኢትዮጵያ ሙዚቃ ፔንታቶኒክ የምንለው ሙዚቃ ነው" የሚለው ግሩም መዝሙር ፓን አፍሪካን ፔንታቶኒክ ፕሮጀክት የምዕራብ እና የምሥራቅ አፍሪቃን ሙዚቃ እንደሚያገናኝ ያስረዳል። "እሱ የራሱ ባህል ውስጥ ሆኖ እኛም የራሳችንን በምንጫወትበት ጊዜ ብዙ ማቀናበር ብዙ መድከም አይጠይቅም። የቋንቋ ገደብ ቢኖርም በቀላሉ በሙዚቃ እንግባባለን" ሲል ስለ ጥምረታቸው ለDW አስረድቷል። 

አልሑሴኒ አኒቮላ በበኩሉ ጥምረታቸው በአፍሪካ እሴቶች ላይ እንደሚያተኩር ገልጿል። ግሩም መዝሙር የጃዝ ሙዚቀኛ ሲሆን ጊታር ይጫወታል። አልሑሴኒ አኒቮላ በመላው ዓለም ዝናን ያተረፈው ደዘርት ብሉዝ የተባለ የሙዚቃ ባንድ መሪ ድምፃዊ እና የጊታር ተጫዋች ነው። የ61 አመቱ ሥመ-ጥር የማንዶሊን ተጫዋች አየለ ማሞ በድሬዳዋው መድረክ ከግሩም እና አልሑሴኒ አኒቮላ ጋር ተጫውቷል።

የድምፅ ማዕቀፉን በመጫን ሙሉ መሰናዶውን ያድምጡ

መሳይ ተክሉ 
እሸቴ በቀለ