1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

በጋምቤ ከትናንት አንስቶ ሰዓት እላፊ ታውጇል።

ሐሙስ፣ ሐምሌ 13 2015

የሰዓት እላፊ ገደቡ የተቀመጠው ሰሞኑን በክልሉ በተከሰተው የጸጥታ ችግር ምክንያት እንደሆነ የክልሉ ኮሙኒኬሽን አስታውቋል። የጽ/ቤቱ ኃላፊ አቶ ኡገቱ አዲንግ ለዶቼቬለ እንደተናገሩት ሰሞኑን በክልሉ በተከሰተው የጸጥታ ችግር የሰዎች ህይወት ማለፉን ተናግረዋል፡፡ በሰው እና ንብረት ላይ የደረሰው የጉዳት መጠን እየተጣራ እንደሚገኝም አክለዋል፡፡

https://p.dw.com/p/4UBKe
 Dima Woreda in Gambela region
ምስል Negassa Desalegn/DW

በጋምቤላ ክልል ሰሞኑን በተከተሰው  የጸጥታ ችግር በሰው ህይወት እና ንብረት ላይ ከፍተኛ ጉዳት መድረሱን የክልሉ መንግስት አስታውቋል፡፡  የጸጥታ ችግሩን ለመቆጣጠር እንዲያመች የሰዓት ዕላፊ ገደብ መጣሉን የክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዩች ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ኡገቱ አዲንግ ለዶቼቬለ ተናግረዋል፡፡  ከትናንት ማታ ጀምሮ ተግባራዊ በተደረገው የሰዓት እላፊ ከምሽቱ 1፡00 ሰዓት እስከ ንጋቱ 12፡00 ከተፈቀደላቸው የጸጥታ ሐይሎች ውጪ ሰው እና ተሽከርካሪ መንቀሰቃስ እንደማይችል ገልጸዋል፡፡ የሰዓት እላፊ ገደቡ ላልተወሰነ ጊዜ የሚቆይ ነው ያሉት ኃላፊው ሰሞኑን "ጨለማን ተገን አደርገው የሚንቀሳቀሱ የታጠቁ ቡድኖች" ጉዳት ማድረሳቸውን ተናግረዋል፡፡  በተከሰተው ግጭት በኢታንግ ልዩ ወረዳ በሰው እና ንብረት ላይ ጉዳት መድረሱን ገልጸው የጉዳት መጠኑ እየተጣራ ነው ብለዋል፡፡ ያነጋርናቸው የጋምቤላ ከተማ ነዋሪዎች ከባለፈው ሰኞ አንስቶ የጸጥታ ችግር ተባበስቦ መቆየቱ እናን ተቋማት ዝግ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

 Dima Woreda in Gambela region
ምስል Negassa Desalegn/DW

የጋምቤላ ክልል መንግስት ካቢኔ የክልሉን የጸጥታ ሁኔታ አስመልክቶ አስቸካይ ጉባኤ ካደረገ በኃላ የሰዓት እላፊ ገደቡ መጣሉን አመልክቷል፡፡ የሰዓት እላፊ ገደቡ የተቀመጠው ሰሞኑን በክልሉ በተከሰተው የጸጥታ ችግር ምክንያት እንደሆነም የክልሉ ኮሙኒኬሽን ጉዳዩች ጽፈት ቤት አመልክተዋል፡፡ የጋምቤላ ክልል ኮሙኒኬሽን ጉዳዩች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ኡገቱ አዲንግ በሰጡን ማብራሪያ ሰሙኑን በክልሉ በተከሰተው የጸጥታ ችግር የሰዎች ህይወት ማለፉን ተናግረዋል፡፡ በሰው እና ንብረት ላይ የደረሰው የጉዳት መጠን እየተጣራ እንደሚገኝም አክለዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የፈደራል እና የክልል የፀጥታ ኃይሎች ተጨማሪ አደጋ እንዳይከሰት በየወረዳው ተሰማርተው እንደሚገኙም ለዲዳብሊው አብራርተዋል፡፡  ለዘመናት አብሮ የኖረ ማህበረሰብን ወደ ግጭት እንዲያመራ ያደረጉ እና በድርጊቱ የተሳተፉ የክልሉ አመራሮች እንዳሉም ገልጸዋል፡፡ በድርጊቱ የተሳተፉ አመራሮች ጉዳይ ተጣርቶ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወሰድም አመልክተዋል፡፡ጋምቤላ ውስጥ የሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች ጥቃት

የጋምቤላ ከተማ ነዋሪ  አቶ ማሙሸት ደረሰ ከባለፈው ሰኞ አንስቶ በተለያዩ ቦታዎች ላይ  ግጭት መከሰቱን ተናግረዋል፡፡ በገበያ ስፍራ በዝርፍያ የተሰማሩ ግለሰቦችም እንደነበሩ አክለዋል፡፡ በገጠርማ ስፍራዎች ደግሞ ቤቶች መቃጠላቸውን እና ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ነዋሪዎች ላይ የሞት እና የመቁሰል አደጋ መድረሱን ተናግረዋል፡፡ በክልሉ የስደተኞች መጠለያ ውስጥ የሚኖሩ ግለሰቦችም በግጭት ውስጥ መሳተፋቸውን የገለጹት ነዋሪው  ግጭቱ የብሔር መልክ ያለው እና በአካባቢው አብሮ በሚኖሩ የአኙዋና ኑኤር ብሔረሰብ መካከል የተፈጠረ አለመግባባት እንደሆነም አብራርተዋል፡፡ በክልሉ እንደ ላረ እና ኢንታግ አካባቢ አሁንም ከፍተኛ ስጋት መኖሩን ጠቀመዋል፡፡ከማክሰኞ አንስቶ የመስሪያ ቤቶችና የንግድ ተቋማት ዝግ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡የጋምቤላ ነጻነት ግንባር ሙሉ በሙሉ ከትጥቅ ትግል መውጣቱን ዐስታወቀ

 Dima Woreda in Gambela region
ምስል Negassa Desalegn/DW

የክልሉ ኮሙኒኬሽን ትናንት ይፋ ባደረገው መረጃ የመንግስት ሰራተኞች እና ተቋማት ከዛሬ ጀምሮ መደበኛ ስራቸውን እንዲጀምሩ ውሳኔ ማሳለፉን ጠቅሷል፡፡  ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ እና ማንኛውንም ድምጽ አልባ መሳሪያ ይዞ መንቀሳቀስ እንደማይችል የክልሉ መንግስት ገልጸዋል፡፡ ይህን ተላልፎ ይዞ የተገኘ ግለሰብ እርምጃ እንደሚወሰድበትም ተጠቁሟል፡፡ በግጭቱ ለደረሰው የሰው ህይወት ህልፈትና ንብረት ውድመት የክልሉ መንግስት የተሰማውን ጥቅል ሀዘን  ገልጸዋል፡፡

ነጋሳ ደሳለኝ

ኂሩት መለሰ

ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር