1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጉራፈርዳ ተፈናቃዮች እሮሮ

ሐሙስ፣ ሰኔ 3 2013

ከደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች መንግሥት መፍትሄ ይስጠን ሲሉ ጠየቁ። ተፈናቃዮቹ አዛው ባሉበት የጉራፈርዳ ወረዳ እየተረዱ እንደሚገኙ ነው የማውቀው የሚለው የደቡብ ክልል የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በበኩሉ ነዋሪዎቹ ቀደም ሲል ወደ መጡበት ዞን ስለመመለሳቸው አስከአሁን ያሳወቀው አካል እንደሌለ ገልጿል።

https://p.dw.com/p/3uij7
Äthiopien Vertriebene in Guraferda
ምስል Shewangizaw Wegayehu/DW

መንግሥት መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀዋል

ከደቡብ ክልል ቤንች ሸኮ ዞን ጉራፈርዳ ወረዳ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች መንግሥት ለደረሰብን ችግር መፍትሄ ይስጠን ሲሉ ጠየቁ። «ሕይወታችን አደጋ ላይ ወድቋል» በማለት ከጉራፈርዳ ወረዳ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ዛሬ ሀዋሳ በሚገኘው የደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት ደጃፍ በመሰባሰብ አቤቱታቸውን አሰምተዋል። ተፈናቃዮቹ አዛው ባሉበት የጉራፈርዳ ወረዳ እየተረዱ እንደሚገኙ ነው የማውቀው የሚለው የደቡብ ክልል የአደጋ ስጋት ሥራ አመራር ኮሚሽን በበኩሉ ነዋሪዎቹ ቀደም ሲል ወደ መጡበት ዞን ስለመመለሳቸው አስከአሁን ያሳወቀው አካል እንደሌለ ገልጿል።

ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ 

ሸዋዬ ለገሠ

ማንተጋፍቶት ስለሺ