የጉማይዴ ሕዝብ አቤቱታ
ዓርብ፣ ታኅሣሥ 16 2013ማስታወቂያ
በደቡብ ክልል የሚገኘው የጉማይዴ ማኅበረሰብ ከፍተኛ የህልውና አደጋ ተጋርጦበታል ሲሉ ተወካዮቹ ተናገሩ። ተወካዮቹ የጉማይዴ ሕዝብ ከመጋቢት 2003 ዓ/ም ጀምሮ በኮንሶ ዞን ሥር እንዲተዳደር የተላለፈውን ውሳኔ በመቃወም በሰላማዊ መንገድ በየደረጃው ለሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ድምጹን ሲያሰማ መቆየቱን ይናገራሉ። ከ2011ዓ/ም ጀምሮ ከ 80 በላይ ሰዎች ሲገደሉ 40 ሺህ ያህል እንደተፈናቀሉ፣ ችግራቸውን ለፌደራል መንግሥት ለማሳወቅ አዲስ አበባ የመጡ የማኅበረሰቡ ተወካዮች ተናግረዋል። ጉዳዩን የሚያጣራ ቡድን መላኩን ያሳወቀው የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽንም ሰዎች በአካባቢው በአሰቃቂ መንገድ መገደላቸውንና ንብረቶችም መውደማቸውን ባወጣው መግለጫ አረጋግጧል። ሰሎሞን ሙጩ ከአዲስ አበባ ተከታዩን ዘገባ አጠናቅሯል።
ሰሎሞን ሙጪ
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ