1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ገበሬዎች መንግሥትን በመቃወም አድማ መቱ

ሰኞ፣ ታኅሣሥ 29 2016

የጀርመን መንግሥት ለገበሬዎች የሚሰጠዉን የእርሻ ድጎማዎችን ለመቀነስ ያወጣውን ዕቅድ ተከትሎ የጀርመን ገበሪዎች በርሊን ላይ ከፍተኛ የተቃዉሞ ሰልፍ ጀምረዋል። በመላ አገሪቱ የመንገድ መዘጋቶች ወደ ተለያዩ ቦታዎች የሚሄዱ ተጓዦችን እያደናቀፈ ነዉ። መዲና በርሊን እምብርት ላይ ገበሪዎች የእርሻ ትራክተራቸዉን ይዘዉ አደባባይ ወጥተዋል።

https://p.dw.com/p/4azHt
የገበሪዎች የተቃዉሞ ሰልፍ በጀርመን
የገበሪዎች የተቃዉሞ ሰልፍ በጀርመን ምስል Nadja Wohlleben/REUTERS

የተቃዉሞ ሰልፉን በግብርና ምርት ስር የተሰማሩ ፤ ዳቦ ጋጋሪዎች፤ የምግብ አቅራቢዎች ፤ የወተት ተዋጽኦ አምራቾች እና የኩባንያ ሰራተኞች ተቀላቅለዉታል።

የጀርመን መንግሥት ለገበሬዎች የሚሰጠዉን የእርሻ ድጎማዎችን ለመቀነስ ያወጣዉን ባወጣው ዕቅድ ተከትሎ የጀርመን ገበሪዎች በርሊን ላይ ከፍተኛ የተቃዉሞ ሰልፍ ጀምረዋል። በመላ አገሪቱ የመንገድ መዘጋቶች ወደ ተለያዩ ቦታዎች የሚሄዱ ተጓዦችን እያደናቀፈ ነዉ። በተለይ መዲና በርሊን እምብርት ላይ ገበሪዎች የእርሻ ትራክተራቸዉን ይዘዉ አደባባይ ወጥተዋል።

ዛሬ ከቀትር በፊት የበርሊን ፖሊስ እንደገለፀዉ በተቃዉሞ ሰልፉ ላሽ 566 ትራክተሮችን፣ የጭነት መኪናዎችን፣ ተሳቢ ተሽከርካሪዎችን መቁጠሩን ገልጿል። በሰላማዊ ሰልፉ ላይ የእርሻ መሳርያ ተሽከርካሪዎቹን ከሚነዱት በተጨማሪ 550 ገበሪዎች እንደሚገኙ ፖሊስ በሰጠዉ መግለጫ አስታዉቋል።  በሌላ በኩል በቱሪንጂያ ግዛት የጀርመን የአገር ውስጥ መረጃ ኃላፊ የቀኝ አክራሪዎች ገበሬዎቹ በፌዴራሉ መንግሥት ላይ የሚሰነዘሩትን ተቃውሞ ለራሳቸው ዓላማ ሊጠቀሙ ይችላሊሉ ሲሉ አስጠንቅቀዋል።

የ2023 ዓ.ም. የጀርመንን የውጭ ፖሊሲ ቅኝትና በ2024 የሚጠበቀው

የተቃዉሞ ሰልፉን በግብርና ምርት ስር የተሰማሩ ፤ ዳቦ ጋጋሪዎች፤ የምግብ አቅራቢዎች ፤ የወተት ተዋጽኦ አምራቾች የመሳሰሉ ባለሞያዎች እና የኩባንያ ሰራተኞች ተቀላቅለዉታል። ከዚህ ሌላ የባቡር አሽከርካሪዎች ተቃዉሞዉን ይቀላቀላሉ ተብሎ ይጠበቃል። ሰላማዊ ሰልፉ ለአንድ ሳምንት እንደሚዘልቅም ተነግሯል።

ይህ ምን ማለት ይሆን። ዛሬ በበጀርመን መዲና በርሊን ላይ የጀርመን ገበሪዎች ያካሄዱት የተቃዉሞ ሰልፍ በተመለከተ በርሊን ላይ የሚገኘዉን ወኪላችንን ይልማ ኃይለሚካኤልን አነጋግረናል።

አዜብ ታደሰ

ማንተጋፍቶት ስለሺ