1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ የአመራር ለውጥ

ሰኞ፣ ግንቦት 26 2011

የጀርመን ሶሻል ዴሞክራቲክ ፓርቲ (SPD) ትላንት ከስልጣናቸው የለቀቁትን የፓርቲው ሊቀመንበር የሚተካ ግለሰብ እስኪመረጥ ድረስ የSPD ሦስት ምክትል ፕሬዝዳንቶች ጊዜያዊ የመሪነት ስፍራውን እንዲረከቡ ውሳኔ አስተላለፈ።  ውሳኔው የተላለፈው የፓርቲው የስራ አስፈጻሚ ቦርድ ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ ነው።

https://p.dw.com/p/3Jllz
SPD Krise Andrea Nahles nach der EU Wahl in Berlin
ምስል Reuters/F. Bensch

ፓርቲ ሊቀመንበር እስኪመርጥ ሦስት ምክትል ፕሬዝዳንቶች ይመሩታል

የጀርመን ሶሻል ዴሞክራት ፓርቲ (SPD) መሪ አንድሪያ ናህሌስ ከፓርቲ መሪነታቸው እንደሚለቁ ትላንት አስታውቀዋል። ናህሌስ ስልጣናቸውን የለቀቁት ፓርቲያቸው አዲስ መሪ እንዲመርጥ ዕድል ለመስጠት እንደሆነ ገልጸዋል። የሊቀመንበሯ ውሳኔ ሶሻል ዴሞክራቶቹ ከሳምንት በፊት በተካሄደው የአውሮፓ ምርጫ የከፋ ውጤት ማስመዘገባቸውን ተከትሎ የመጣ ነው።

ናህሌስን ማን ይተካ ይሆን? ከሚለው ጥያቄ ጎን ለጎን SPD ዋነኛ ተጣማሪ በሆነበት የጀርመን ጥምር መንግስት ላይ ውሳኔው የሚያሳድረው ተጽዕኖ አጠያይቋል። የSPD ሊቀመንበር ከስልጣን መልቀቅ የጀርመን ጥምር መንግስትን እንዳያፈርሰው ተሰግቷል። የጊዜ ጉዳይ ነው እንጂ SPD በጎርጎሮሳዊው 2021 ከሚካሄደው አጠቃላይ ምርጫ በፊት ከጥምር መንግስት ውስጥ መውጣቱ የማይቀር ነው የሚሉ የፓርቲው ሰዎች አሉ።   

በጉዳዩ ላይ ከበርሊኑ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኃኤል ጋር ያደረግነውን ቃለ ምልልስ ለማድመጥ የድምጽ ማዕቀፉን ይጫኑ።   

ይልማ ኃይለሚካኃኤል/ ተስፋለም ወልደየስ 

ማንተጋፍት ስለሺ