1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የጀርመን መሰረታዊ ሕግጋቶች ምስረታ 75ኛ ዓመት አከባበር

ሐሙስ፣ ግንቦት 15 2016

የጀርመን መተዳደርያ መሰረታዊ ሕግጋቶች 75ኛ ዓመት ምስረታ ዛሬ ጀርመን መዲና በርሊን ላይ በድምቀት ተከበረ። እለቱ በወታደራዊ የክብር ዘበኛ ሰልፍ ጨምሮ በተለያዩ ዝግጅቶች የጀርመን ፓርላማ ቡንደስታግ ፕሬዝዳንት እና የጀርመኑ መራሄ መንግሥትን ጨምሮ የተለያዩ ክልሎች ባለስልጣናት እና ወጣቶች በተገኙበት ተከብሯል።

https://p.dw.com/p/4gCYK
በርሊን፤ የጀርመን መሰረታዊ ሕግ ምስረታ 75ኛ ዓመት አከባበር
በርሊን፤ የጀርመን መሰረታዊ ሕግ ምስረታ 75ኛ ዓመት አከባበር ምስል Kay Nietfeld/dpa/picture alliance

በርሊን፤ የጀርመን መሰረታዊ ሕግጋቶች ምስረታ 75ኛ ዓመት አከባበር

የጀርመን መተዳደርያ መሰረታዊ ሕግጋቶች ዛሬ በጀርመን በተለይ ደግሞ መዲና በርሊን ላይ በድምቀት ተከበረ። ፕሬዝዳንት ፍራንክ ቫልተር ሽታይንማየር እለቱ በወታደራዊ የክብር ዘበኛ ሰልፍ እንዲሳተብ ትዕዛዝ ባስተላለፉት መሰረት፤ ዛሬ ቀትር ላይ የጀርመን ፓርላማ ቡንደስታግ ፕሬዝዳንት ባረቤል ባስ፣ የጀርመኑ መራሄ መንግሥት ኦላፍ ሾልዝ፣ የጀርመን ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ማኑዌላ ሽዌሲግ እና የፌደራል ህገ መንግስታዊ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ስቴፋን ሃርባርትን ጨምሮ የፌደራል ጀርመን መንግስት አባላትና የጀርመን ክልል ባለሥልጣናት ፣ የአገራት ዲፕሎማቲክ ተወካዮች እና ከጀርመን ፌዴራላዊ ክልሎች የተጋበዙ ወጣቶች በተገኙበት በደማቅ ታስቦ ዉሏል። በዝግጅቱ ላይ የቀድሞዋ መራሂተ መንግሥት አንጌላ ሜርክል እና መራሂተ መንግስት ጌሃር ሽሮደር እንዲሁም ከናዚ የግፍ ጭፍጨፋ የተረፉ ሰዎች ተገኝተዋል። የጀርመን መሠረታዊ ሕግ የፀደቀበት 75ኛ ዓመት ዛሬ ታስቦ ሲዉል የሃገሪቱ ሰንደቃላማ  በመላው ጀርመን በሚገኙ የፌዴራል ባለ ሥልጣናት መስርያ ቤቶች እና ድርጅቶች ብሎም ሕጋዊ እና መንግስታዊ ሕንፃዎች ላይ ተዉለብልበዋል። የጀርመን መሰረታዊ ሕግ ድንጋጌ 75 ኛ ዓመት ክብረ በዓል በሳምንቱ መጨረሻ በተለያዩ ዝግጅቶች በተለይ በርሊን ላይ እንደሚቀጥል የወጡ መረሃ-ግብሮች ይጠቁማሉ። በበርሊን የተካሄደዉን አከባበር በተመለከተ ቦታዉ ላይ የሚገኘዉ ወኪላችን ይልማ ኃይለሚካኤል ጠይቀነዋል። 

ይልማ ኃይለሚካኤል 
አዜብ ታደሰ 
ማንተጋፍቶት ስለሺ