1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዶቼቬለ ዓለምአቀፍ የመገናኛ ብዙኀን ዓመታዊ ስብሰባ

ሐሙስ፣ ሰኔ 16 2014

<< ነገን ዛሬ እንቅረጸው>> በሚል መርህ በተካሄደው አለምአቀፍ ጉባኤ ከበርካታ አገራት የመጡ ጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዜኀን ባለሙያዎች ተሳትፏል። የDW ዋና ዳይሬክተር ሚስተር ፒተር ሊምቡርግ በጉባኤው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት አስተላልፏል።

https://p.dw.com/p/4D8XZ
DW Global Media Forum | Der äthiopische Journalist Henok Semaegziher
ምስል privat

የDW አለምአቀፍ የመገናኛ ብዙኀን ዓመታዊ ስብሰባ

DW በየዓመቱ ቦን ዉስጥ የሚያስተናግደዉና ለለፉት 3 ዓመታት በኮረና ወረርሽኝ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው  የመገናኛ ብዙኀን አለምአቀፍ ዓመታዊ ጉባኤ (ወይም ፎረም) ሁለት ዩክሬናውያን ጋዜጠኞችን በመሸለም ተጠናቋል።
ባለፈዉ ሰኞና ማክሰኞ በተካሔደዉ  ጉባኤ ከኢትዮጵያ የDW አካዳሚ ባልደረባ ሚክያስና የቀድሞው የVOA ባልደረባ አሁን የመርሳ የመገናኛ ብዙሃን ስልጠናና ምርምር ተቋም መስራችና ሃላፊ ሄኖክ ሰማእግዚሄር ተሳታፊ ነበሩ።ሁለቱ  በከDW የአማርኛው ክፍል ባልደርቦች ጋርም ትናንት አጭር ዉይይት አድርገዋል።
<< ነገን ዛሬ እንቅረጸው>> በሚል መርህ በተካሄደው አለምአቀፍ ጉባኤ ከበርካታ አገራት የመጡ ጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዜኀን ባለሙያዎች ተሳትፏል። የDW ዋና ዳይሬክተር ሚስተር ፒተር ሊምቡርግ በጉባኤው የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት አስተላልፏል። በስብሰባው ከተሳተፉት የቀድሞው የVOA ባልደረባ አሁን የመርሳ የመገናኛ ብዙሃን ስልጠናና ምርምር ተቋም መስራችና ሃላፊ ሄኖክ ሰማእግዚሄርጋ  ጠቃሚ ጉዳዮች ማግኘቱን በሰጠንን አስተያየት ተናግሯል።

በኢትዮጵያ ጋዜጠኞችና የመገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች እስር በመገናኛ ብዙሃን ስራና በመናገር ነጻነት ላይ ትልቅ ደንቃራ እንደተፈጠረ የመስኩ የመብት ተሟጋቾች ይከራከራሉ። ይህ በጋዜጠኝነት ስራ ፈታኝ አይሆንም ወይ አልነው ሄኖክ ሰማእግዚሄርን። የጋዜጠኞች እስር በሙያው ላይ ጫና እንዳለው በመግለጽ በሂደት ቀስ ቀስ እየተለወጠ እንደሚሄድ ተስፋ እንዳለው ገልጿል።
በስተመጨረሻም ከቢሮአችን በቅርብ ርቀት የሚገኘውን በግዙፉ የራየን ወንዝ «ተቀንታ» የምትገኘውን ጥንታዊት የቦን ከተማጥሩ ግዜ እንዳሳለፈ ነግሮናል።
ሄኖክ ሰማ እግዚሄርና ሚክያስ ከDW አማርኛ ክፍል ባልደረቦች ጋም ቢሮውስ ተገናኝተው አጭር የሐሳብ ልውውጥ አድርጓል። 

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሔር 

ነጋሽ መሐመድ