የዶክተር ዐብይ እና የምሁራን ውይይት
ሰኞ፣ ሐምሌ 16 2010ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ ዛሬ ከ50 የተለያዩ ከፍተኛ የትምሕርት ተቋማት ከተወከሉ ሦስት ሺህ አንድ መቶ ሰባ አምስት 3175 መምህራን ጋር የካሄዱት ውይይት በተሳታፊዎች የተለያዩ አስተያየቶች ተሰጥቶበታል። መምህራኑ በውይይቱ ወቅት ላነሷቸው የተለያዩ ጥያቄዎች ጠቅላይ ሚኒስትሩ መልስ ሰጥተዋል። በተለያየ ምክንያት ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የተባረሩ 42 ምሁራንን ለመመለስ መንግሥት ዝግጁ መሆኑንም ተናግረዋል። ዶቼቬለ ካነጋገራቸው ተሳታፊዎች አንዱ ውይይቱን « ግልጽ እና ውጤታማ» ብለውታል። እንደረኩበትም ተናግረዋል። ሌላው አስተያየት ሰጭ ደግሞ የተነሱት ጥያቄዎች «ምሁራዊም ሆነ አገራዊ አይደሉም»ሲሉ ነቅፈዋል። ይልቁንም በዩኒቨርስቲ ደረጃ ሊፈቱ የሚችሉ እንደነበሩ እና በውይይቱም እንዳልተደሰቱ የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ያነጋገራቸው ገልጸዋል።
ዮሐንስ ገብረ እግዚአብሔር
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ