የድንበር ተሻጋሪ ሾፌሮች ቅሬታ
ዓርብ፣ ግንቦት 21 2012ማስታወቂያ
በስራችን ምክንያት ጅቡቲ ደርሰን ስንመለስ ህብረተሰቡ በቤተሰቦቻችን ላይ ሳይቀር መገለል እየደረሰብን ነው ሲሉ የድንበር ተሻጋሪ ከባድ መኪና ሾፌሮች ተናገሩ።በተለይ የጤና ሚኒስቴር በኮሮና ተኅዋሲ የሚያዙ ሰዎችን ሲገልጽ የእኛን ሙያ ጠቅሶ ሪፖርት ማድረጉ የምናጓጉዘውን ሸቀጥ በምናቀርብለት ማህበረሰብ እንድንገፋ እያደረገን በመሆኑ ሊታረም ይገባል ብለዋል።
መንግስት በበኩሉ እነዚህ አሽከርካሪዎችና ቤተሰቦቻቸው ከበሽታው እንዲጠበቁ በቀጣይ ስራዎች ይከናወናሉ ብሏል።ሰሎሞን ሙጬ ከአዲስ አበባ ዝርዝሩን ልኮልናል።
ሰሎሞን ሙጬ
ኂሩት መለሰ
ነጋሽ መሐመድ