1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የድሬዳዋ የምርጫ ዝግጅት 

ቅዳሜ፣ ሰኔ 12 2013

የድረደዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮምሽን ኮምሽነር አለሙ መግራ በበኩላቸው በሰጡት መግለጫ ፖሊስ የምርጫ ቁሳቁሶችን ወደ ምርጫ ጣቢያ አጅቦ የማጓጓዝ ስራ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው በምርጫው ዕለትም ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ለመስራት አስፈላጊውን ዝግጅት አድርጓል ብለዋል ፡፡

https://p.dw.com/p/3vDqJ
Äthiopien | Wahlen | Ato Zyad Yasin
ምስል Mesay Tekilu/DW

የድሬዳዋ የምርጫ ዝግጅት 

ከነገበስቲያ ለሚካሄደው 6ኛው ሀገር አቀፍ ምርጫ አስፈላጊ የምርጫ ቁሳቁሶች ሙሉ በሙሉ መድረሳቸውን የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ድሬደዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት አስታወቀ።
የብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ድሬደዋ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ሓላፊ አቶ ዚያድ ያሲን ለሚዲያ በሰጡት መግለጫ በመስተዳድሩ የከተማና የገጠር ቀበሌዎች ላሉ አርባ ሰባት የምርጫ ክልሎች የሚያስፈልግ የምርጫ ቁሳቁስ መድረሱንና ከምርጫው ቀን አስቀድሞ ወደ ምርጫ ጣቢያዎች የማጓጓዝ ስራ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡
የቦርዱ ቅርንጫፍ ፅ/ቤት ኃላፊ አቶ ዚያድ በአስተዳደሩ ከተማና ገጠር ባሉ ሁለት መቶ ሃምሳ ዘጠኝ የምርጫ ጣቢያዎች ምርጫ ለሚያስፈፅሙ አካላትም ስልጠና በመስጠት ዝግጅት መደረጉን አስረድተዋል፡፡
የድረደዋ አስተዳደር ፖሊስ ኮምሽን ኮምሽነር አለሙ መግራ በበኩላቸው በሰጡት መግለጫ ፖሊስ የምርጫ ቁሳቁሶችን ወደ ምርጫ ጣቢያ አጅቦ የማጓጓዝ ስራ እየሰራ መሆኑን ጠቅሰው በምርጫው ዕለትም ከሌሎች የፀጥታ አካላት ጋር በመቀናጀት ለመስራት አስፈላጊውን ዝግጅት አድርጓል ብለዋል ፡፡
ኮምሽነሩ በምርጫው ዕለትም ሆነ በድህረ ምርጫው ምንም ዓይነት የፀጥታ ስጋት ይገጥማል የሚል እምነት እንደሌላቸው ጠቁመዋል፡፡
ለፌደራል እና ለድሬደዋ አስተዳደር ምክር ቤት ህዝብ እንደራሴዎችን ለመምረጥ በሚካሄደው ምርጫ ህብረተሰቡ ይበኛል ያለውን በመምረጥ እንዲሳተፍ በብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ድሬደዋ ቅርንጫፍ ፅበ/ት ጥሪ ቀርቧል፡፡

መሳይ ተክሉ

ኂሩት መለሰ