የደቡብ ክልል ጉባኤ
ዓርብ፣ መጋቢት 9 2014ማስታወቂያ
በደቡብ ክልል የሚነሱ የአደረጃጀት ጥያቄዎችን ለመመለስ እየሠራ እንደሚገኝ የክልሉ ምክር ቤት አስታወቀ። የክልሉ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ፋጤ ሰርሞላ ይኽን የተናገሩት ዛሬ በሀዋሳ ከተማ በተጀመረው የምክር ቤቱ ስድስተኛ ዙር አንደኛ መደበኛ ጉባኤ ላይ ነው። አፈ ጉባኤዋ በመክፈኛ ንግግራቸው በክልል ለመደራጀት ጥያቁ ያቀረቡ ሕዝቦች ባልተረጋገጠ ወሬ እና ውዥንብር ሳይደናገሩ ምላሹን በትዕግሥት ሊጠብቁ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ሸዋንግዛው ወጋየሁ
ሸዋዬ ለገሠ
ኂሩት መለሰ