1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደቡብ ክልል እጣ ፈንታ

እሑድ፣ ሰኔ 21 2012

የወላይታ ዞን ፣ክልላዊ መንግሥት ለመመስረት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አስታውቋል።16 ብሄር ብሄረሰቦች የሚገኙበት የደቡብ ኦሞ ዞን ብቻውን ክልል ሆኖ እንዲደራጅ በዚህ ሳምንቱ አስቿኳይ ጉባኤው ወስኗል። ሌሎች ዞኖችም በተመሳሳይ ሁኔታ ክልሉ ለአራት መከፈሉን እንማይቀበሉት እየገለጹ ነው።

https://p.dw.com/p/3eRZQ
Äthiopien SNNPR Konferenz zur Sidama-Zone
ምስል DW/S. Wegayehu

የደቡብ ክልል እጣ ፈንታ

ሁለት ዓመት ካስቆጠረው የኢትዮጵያ ለውጥ ወዲህ ፣በደቡብ ክልል የሚገኙ የአሥራ ሁለት ዞኖች ምክር ቤቶች ያቀረቡት  በክልል የመደራጀት ጥያቄ ከሲዳማ በስተቀር የሌሎቹ እልባት አላገኘም። በመፍትሄ ፍለጋው ሂደት የጠቅላይ ሚኒስትር ዓቢይ አህመድ መንግሥት ክልሉን በአራት ከፍሎ ለማደራጀት ያቀረበው ምክረ ሃሳብ በክልሉ ፖለቲከኞች እና የሃገር ሽማግሌዎች እየተመከረበት ነው።ሆኖም የሲዳማ ዞን አሥረኛው ክልል ከሆነበት ካለፈው ሳምንት ወዲህ በክልል የመደራጀት ጥያቄ ያቀረቡት ሌሎች ዞኖች ፣ጥያቄዎቹ እንዴት ይፈቱ በሚል ሲመክር የቆየው የሰላም አምባሳደሮች ቡድን አቀረበ የተባለውን ምክረ ሃሳብ ተቃውመው ጥያቄአቸው መልስ እንዲያገኝ ግፊታቸውን አጠናክረዋል።ከመካከላቸውም የወላይታ ዞን ፣ክልላዊ መንግሥት ለመመስረት እየተንቀሳቀሰ መሆኑን አስታውቋል።16 ብሄር ብሄረሰቦች የሚገኙበት የደቡብ ኦሞ ዞን ብቻውን ክልል ሆኖ እንዲደራጅ በዚህ ሳምንቱ አስቿኳይ ጉባኤው ወስኗል። ሌሎች ዞኖችም በተመሳሳይ ሁኔታ ክልሉ ለአራት መከፈሉን እንማይቀበሉት እየገለጹ ነው።ከዚህ በመነሳትም የሲዳማ ክልል ከተቋቋመ በኋላ 55 ብሄረሰቦችን በውስጡ የያዘው የደቡብ ክልል  እንዴት ይቀጥል የሚለው ጥያቄ ማነጋገሩና ማሳሰቡ ቀጥሏል።የዛሬው እንወያይ በዚህ ላይ ያተኩራል። በጉዳዩ ላይ የሚወያዩ አራት እንግዶችን ጋብዘናል እነርሱም አቶ ደያሞ ዳሌ በደቡብ ብሔር ብሄረሰቦች ክልል የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ከፍተኛ ባለሞያ ረዳት ፕሮፌሰር ሽመልስ አሻግሬ በሃዋሳ ዩኒቨርስቲ የሕግ መምህር፣ረዳት ፕሮፌሰር ዳንኤል መኮንን በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ የፖለቲካ ሳይንስ መምህር እንዲሁም አቶ አሸናፊ ከበደ የወላይታ መብት ተሟጋች ናቸው።ሙሉውን ውይይት ለመከታተል ከታች የሚገኘውን የድምጽ ማዕቀፍ ይጫኑ።

ኂሩት መለሰ