1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የደቡብ ሱዳናውያኑ ስደተኞች ኑሮ በኢትዮጵያ

እሑድ፣ ጥር 5 2011

ደቡብ ሱዳን ወደ ለየለት የእርስ በእርስ ጦርነት ከገባችበት ጊዜ ወዲህ በ10 ሺህ የሚቆጠሩት ዜጎቿ አልቀዋል፡ 4 ሚሊዮን ያህሉም ለስደት ተዳርገዋል፡፡ በዚህ ጊዜ ውስጥ 423 ሺሕ ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ በመግባት ጋምቤላ ልል ውስጥ በሚገኙ 6 የስደተኛ ካምፖች ውስጥ ተጠልለዋል፡፡

https://p.dw.com/p/3BUZh
Flüchtlinge aus dem Südsudan in Äthiopien
ምስል DW/S. Muchie

የደቡብ ሱዳናውያኑ ስደተኞች ኑሮ በኢትዮጵያ

በመጠለያ ካምፖቹ እድሜያቸው ከ 18 አመት በታች የሆናቸው ህጻናትና ሴቶች በብዛት ይገኛሉ፡፡ የስደተኞች ቁጥር መጨመር የማህበራዊ ግልጋሎት ፍጎቶችን አሳድጎታል። የጋምቤላ ክልላዊ መንግሥት የሚያስተዳድረው ተጨማሪ 1 የስደተኞች ካምፕ የሚገኝ ሲሆን ከ 15 በላይ ሃገር በቀል እና የውጭ መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች ከኢትዮጵያ ምንግስትና ተባበሩት መንግስታት ጋር በመተባበር ለስደተኞች የደህንነት ጥበቃ ፣ የምግብ ፣ የውሃ ፣ የመጠለያ እና የትምህርት አገልግሎት ይሰጣሉ። 
መንግስት በእነዚህ የስደተኛ ካምፖች ውስጥ የጸጥታ ችግር እንዳይቀሰቀስ እና ግጥቶች እንዳይፈጠሩ ጥብቅ ቁጥጥር እና ክትትል እያደረገ እንደሚገኝ አስታውቋል፡፡
ኢትዮጵያ ከ 12ኛው መቶ ክፍለዘመን ጀምሮ ስደተኞችን ተቀብላ የምታስተናግድ ሃገር ስትሆን በአሁኑ ወቅትም ከተለያዩ 1 ሃገሮች የመጡ 905  ሽህ ስደተኞችን አስጠልላለች፡፡
ሰለሞም ሙጬ
እሸቴ በቀለ