የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝበ-ውሳኔ ሲካሔድ ዋለ
ሐሙስ፣ መስከረም 20 2014ማስታወቂያ
የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ሕዝቦች የደቡብ ክልል አካል ሆነው ለመቀጠል ወይም በአዲስ ክልል ለመደራጀት ያስችለናል ያሉትን የህዝበ ውሳኔ ድምፅ ሲሰጡ ውለዋል ።
በህዝበ ውሳኔው ውጤት መሰረት የጋራ ክልል ለመመሥረት የሚያበቃቸውን ድምፅ ካገኙ የፌድራላዊ ሪፐብሊኩ አስራ አንደኛ ክልል ሆነው የሚደራጁ ይሆናል ።
የኢትዮጲያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ በበኩሉ የህዝበ ውሳኔ ድምፅ አሰጣጥ ሂደት በጥቂት የድምፅ መስጫ ጣቢያዎች ከታየው የታዛቢዎች መዘግየት በስተቀር የለምንም ችግር መካሄዱን አስታውቋል።
ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ
እሸቴ በቀለ
አዜብ ታደሰ