የዩክሬን ሩሲያ ፍጥጫና የጦርነት ስጋት
ረቡዕ፣ የካቲት 16 2014ማስታወቂያ
የሩሲያ ወረራ ያሰጋኛል ያለችው ዩክሬን ለ30 ቀናት የሚዘልቅ የአስጠኳይ ጊዜ አዋጅ ለመደንገግ መዘጋጀቷ ተሰምቷል። በድንጋጌው መሠረት ዩክሬናውያን በቤት ተወስነው እንዲቆዩ ወይም የሰዓት እላፊ ሊከተል እንደሚችል ተገምቷል። ሩሲያ ከዩክሬን ለመገንጠል የሚንቀሳቀሱ ሁለት ግዛቶች እውቅና መስጠቷ በሁለቱ ሃገራት መካከል የተጀመረው እሰጥ አገባ ይበልጥ አክርሮታል እየተባለ ነው። ሩሲያ ከዩክሬን ለመገንጠል የሚንቀሳቀሱ አማጽያንን መደገፏን የተቃወመው የአውሮጳ ሕብረት ማዕቀብ የጣለ ሲሆን ከአሜሪካ ወገንም ተመሳሳይ ርምጃዎች መኖራቸው ተገልጿል። ምዕራቡ ዓለም በሩሲያ ላይ ጫና ለማሳደር የሚወስዳቸው የማዕቀብ ርምጃዎች ሁኔታውን እንዳያባብሱት የሚሰጉ አሉ።
ይልማ ኃይለ ሚካኤል
ሸዋዬ ለገሠ
ነጋሽ መሐመድ