1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩናይትድ ስቴትስ የፍልሰት መርህ ማሻሻያዎች

ዓርብ፣ መጋቢት 24 2013

በፕሬዝዳንት ጆባይደን አስተዳደር ተግባራዊ ይሆናሉ የተባሉት ማሻሻያዎች ለኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያን የተሻለ ዕድል እንደሚፈጥሩላቸው ዶቼቬለ ያነጋገራቸው አንድ የሕግ ባለሞያ ገልጸዋል።የሕግ ባለሞያው እንዳሉት ጆባይደን በሚወስዷቸው እርምጃዎች በትራምፕ አስተዳደር ይጓተቱ የነበሩ አሠራሮች ሲቀላጠፉ ኢትዮጵያውያኑ ተጠቃሚ ይሆናሉ።

https://p.dw.com/p/3rWw3
USA Joe Biden | Erste PK im Weißen Haus
ምስል Chip Somodevilla/Getty Images/AFP

የዩናይትድ ስቴትስ የፍልሰት መርህ ማሻሻያዎችና ኢትዮጵያውያን

አዲሱ የዩናይትድ ስቴትስ አስተዳደር ሥልጣን እንደያዘ ቃል የገባው የፍልሰት መርህ ማሻሻያዎች በቀድሞ የሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ዘመን የተገን ጥያቄአቸው ተመልካች ላላገኘ ስደተኞች ተስፋ ሰጥቷል። እነዚህ  በፕሬዝዳንት ጆባይደን አስተዳደር ተግባራዊ ይሆናሉ የተባሉት ማሻሻያዎች ለኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያ የተሻለ ዕድል እንደሚፈጥሩላቸው ዶቼቬለ ያነጋገራቸው አንድ የሕግ ባለሞያ ገልጸዋል። የሕግ ባለሞያው እንዳሉት ጆ ባይደን በሚወስዷቸው እርምጃዎች በትራምፕ አስተዳደር ይጓተቱ የነበሩ አሠራሮች ሲቀላጠፉ ኢትዮጵያውያኑ ተጠቃሚ ይሆናሉ። ስለ ዩናይትድ ስቴትስ  የፍልሰት ፖሊሲ ማሻሻያዎች ይዘትና ጠቀሜታ የሕግ ባለሞያውን ያነጋገረው የአትላንታው ዘጋቢያችን ታሪኩ ኃይሉ ተከታዩን ዘገባ አዘጋጅቷል። 
ታሪኩ ኃይሉ 
ኂሩት መለሰ
ሸዋዬ ለገሠ