1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩናይትድ ስቴትስ የጉዞ ማስጠንቀቂያ በጎንደር

ሰኞ፣ ሚያዝያ 23 2009

ዩናይትድ ስቴትስ በሰሜን ኢትዮጵያ ጎንደር ከተማ በተደጋጋሚ የቦምብ ፍንዳታ መከሰቱን በመግለጥ ዜጎቿ ወደ ከተማዪቱ በዚህ ወቅት የመጓዛቸው አስፈላጊነትን በጥንቃቄ እንዲያጤኑ መክራለች።

https://p.dw.com/p/2cC65
Äthiopien historische Ruinen in Gondar
ምስል picture-alliance/dpa/S. Reboredo

Ber.DC. (US travel warning in north Ethiopia) - MP3-Stereo

ዩናይትድ ስቴትስ በሰሜን ኢትዮጵያ ጎንደር ከተማ በተደጋጋሚ የቦምብ ፍንዳታ መከሰቱን በመግለጥ ዜጎቿ ወደ ከተማዪቱ በዚህ ወቅት የመጓዛቸው አስፈላጊነትን በጥንቃቄ እንዲያጤኑ መክራለች።  አዲስ አበባ የሚገኘው የዩናይትድ ስቴትስ ኤምባሲ ሐሙስ ዕለት ባወጣው የጉዞ ማስጠንቀቂያው ጎንደር ከተማ ውስጥ በተደጋጋሚ ቦንብ ፈንድቶ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን ጠቅሷል።

ኤምባሲው የጉዞ ማስጠንቀቂያ ሲያወጣም ይኽ የመጀመሪያው አይደለም። በዩናይትድ ስቴትስ ውጭ ጉዳይ ሚኒሥቴር የአፍሪቃ ጉዳይ ቃል አቀባይ ለዶይቸ ቬለ እንደገለጡት በአካባቢው የሚታዩት ምልክቶች ሰላማዊ ሰልፎችም ሊያስከትሉ ስለሚችሉ ለዜጎቻችን የደህንነት  ስጋቶች ናቸው ብለዋል። አሜሪካ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ የደኅንነት ማስጠንቀቂያ መግለጫውን አስተባብሏል። አንድ የፖለቲካ ተንታኝ ምሁር በበኩላቸው የአሜሪካ የጉዞ ማስጠንቀቂያ በኢትዮጵያ አሉታዊ ገጽታ ይፈጥራል ብለዋል።

መክብብ ሸዋ 

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ሸዋዬ ለገሰ