ትምህርትአፍሪቃ
የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ከትግራይ ወጡ
ማክሰኞ፣ ነሐሴ 11 2013ማስታወቂያ
በትግራይ ክልል በሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች ይማሩ የነበሩ ተማሪዎች ሙሉ በሙሉ ወደየ ቤተሰቦቻቸው መሸኘታቸውን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር በሳምንቱ ማብቂያ አሳውቋል።ትግራይ ዉስጥ የሚደረገዉ ጦርነት ያሰጋቸዉ የተማሪዎቹ ወላጆችና ቤተሰቦች፣ መንግስትና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ተማሪዎቹን ከክሉ ያስወጡላቸዉ ዘንድ በአደባባይ ሰልፍ ጭምር ጠይቀዉ ነበር።ይሁንና በፀጥታ መደፍረስ ምክንያት ተማሪዎቹ በተፈለገዉ ፍጥነት ከትግራይ ክልል አለመዉጣታቸዉ ሥጋት አስከትሎ ነበር።የሳይስና ከፍተኛ ትምሕርት ሚኒስቴር ባለፈዉ ሳምንት አርብ እንዳስታወቀዉ ግን ካለፈዉ ሐምሌ መጀመሪያ ጀምሮ መቀሌ፣አዲግራት፣ አክሱምና ራያ ዩኒቨርስቲዎች ይማሩ የነበሩ ከ10 ሺሕ በላይ ተማሪዎች ከየአካባቢዉ ወጥተዋል።
ሰለሞን ሙጬ
ነጋሽ መሐመድ
አዜብ ታደሰ