1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዩኒቨርሲቲዎች አለመረጋጋት በኢትዮጵያ

እሑድ፣ ታኅሣሥ 26 2012

ካለፉት ሦስት ዐሥርተ ዓመታት ወዲህ ግን የብሔር ፖለቲካ ጎልቶ በመውጣት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ዘንድም ጎራ ለይቶ የመጋጪያ ሰበብ መኾኑ ይጠቀሳል። ባለፉት ወራት ደግሞ ችግሩ ጸንቶ ዩኒቨርሲቲዎች ከዕውቀት መገበያያነታቸው የወጡ መስለዋል። ሕይወትም ጠፍቶባቸዋል።

https://p.dw.com/p/3VhDu
Äthiopien Campus der Assosa Universität
ምስል DW/N. Desalegn

አንዳንዶቹ ለመዝጋት ማስጠንቀቂያ አውጥተዋል

ኢትዮጵያ ከ1950ዎቹ እና 60ዎቹ አንስቶ የሀገሪቱ የፖለቲካ ትኩሳት መጠኑ ይለያይ እንጂ በከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ውስጥም ሲንጸባረቅ ይስተዋላል። በተለይ ካለፉት ሦስት ዐሥርተ ዓመታት ወዲህ ግን የብሔር ፖለቲካ ጎልቶ በመውጣት በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ተማሪዎች ዘንድም ጎራ ለይቶ የመጋጪያ ሰበብ መኾኑ ይጠቀሳል። ባለፉት ወራት ደግሞ ችግሩ ጸንቶ ዩኒቨርሲቲዎች ከዕውቀት መገበያያነታቸው የወጡ መስለዋል።

ከሰሞኑ በኢትዮጵያ አንዳንድ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በደህንነት ችግር የተነሳ የተዘጉ ሲኾን፤ አንዳንዶቹ ለመዝጋት ማስጠንቀቂያ አውጥተዋል። በተለይ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የአንድ አካባቢ ተማሪዎች ተለይተው ከግቢው ለቀው እንዲወጡ የሚያስጠነቅቅ ጽሑፍ ከተለጠፈ እና የአንድ ተማሪ ሕይወት ካለፈ በኋላ ዩኒቨርሲቲው ተዘግቷል። ሌሎች ዩኒቨርሲቲዎችም ተማሪዎቻቸው እንዲህ ካለው  ግጭት ርቀው ወደ ትምህርት ገበታቸው በአስቸኳይ እንዲገቡ አለዚያም ሊዘጉ እንደሚችሉ እያስጠነቅቁ ነው።

ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ዘላቂ ሰላም ሰፍኖ መደበኛ የመማር ማስተማሩ ሒደት እንዲቀጥል ለማድረግ በዋናነት ምን ሊደረግ ይገባል? የውይይቱ ዐቢይ ርእስ ነው።

ሙሉ ውይይቱ የድምፅ ማእቀፉ ውስጥ ይገኛል።

ማንተጋፍቶት ስለሺ

ነጋሽ መሐመድ