1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የየካቲት 26 ቀን 2010 ዓ.ም. የዜና መጽሔት

Tesfalem Waldyes Eragoሰኞ፣ የካቲት 26 2010

በዕለቱ የዜና መጽሔታችን ቀዳሚ የምናደርገው ከዛሬ ጀምሮ ለሶስት ቀናት በኦሮሚያ የተጠራው የስራ ማቆም አድማን ተከትሎ የተለያዩ ከተሞች ውሎ ይሆናል፡፡ ዛሬ ከዝዋይ ማረሚያ ቤት የተለቀቁትን የቀድሞ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬን አነጋግረናል። ስልጣናቸውን መልቀቃቸውን ካሳወቁት ከጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ኃይለማርያም ደሳለኝ የመሪነት መንበሩን ይረከባሉ የተባሉ የገዢው ፓርቲ ባለስልጣናትን የፖለቲካ ሰብዕና ስናስተዋውቃችሁ ቆይተናል፡፡ የደኢህዴን ሊቀመንበርነትን ባለፈው ሳምንት የተረከቡትን የአቶ ሽፈራው ሽጉጤን ማንነት ለዛሬ እናስቃኛችኋለን፡፡

https://p.dw.com/p/2tjhW