1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የየካቲት 14 ቀን 2010 ዓ.ም. ዜና መጽሔት

Tesfalem Waldyes Eragoረቡዕ፣ የካቲት 14 2010

ዛሬ ይፋ የተደረገው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መመሪያ በዕለቱ የዜና መጽሔት ቀዳሚው ነው፡፡ የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ትላንት ለውጭ ሀገር ዲፕሎማቶች “በሀገሪቱ የጸጥታ ስጋት እንደሌለ” መናገራቸው ጥያቄ ጭሯል፡፡ የኢትዮጵያን የፖለቲካ ቀውስ ለመፍታት ሰላማዊ ሽግግር እንደሚያስፈልግ ምሁራን ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል፡፡ ስለፖለቲካ ቀውሱ ሶስት የተቃዋሚ ፓርቲዎች የሰጧቸውን መግለጫዎችንም ይዘናል፡፡ ኢትዮጵያ የግብርና ውጤቶች የድህረ ምርት አያያዝን የሚመራ ሰነድ አዘጋጅታለች፡፡ ፊሊፒንስ በኩዌት በቤት ሰራተኝነት የሚያገለግሉ ዜጎቿ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ማድረጓንም እንዳስሳለን፡፡

https://p.dw.com/p/2t6U8