1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዘሄግ የቀይ ሽብር ችሎት የዛሬ ዉሎ

ረቡዕ፣ ጥቅምት 29 2010

በደርግ ዘመን ጎጃም ክፍለ ሀገር ዉስጥ ባለስልጣን የነበሩት እና አሁን ኔዘርላንድ የሚኖሩት የመቶ አለቃ እሸቱ ዓለሙ ጉዳይ ዛሬም በፍርድ ቤት ሲታይ ዉሏል። ግለሰቡ በስልጣን ዘመናቸዉ ጎጃም ዉስጥ የመንግሥት ፖለቲካ ተዋዋሚዎች ላይ ፈጽመዋል፤ በሚል በርካታ ክሶች ቀርበዉባቸዋል።

https://p.dw.com/p/2nI3o
Symbolbild Justitia Justizia
ምስል Imago

የዕድሜ ልክ እስራት ተጠይቋል፤

 ዘሄይግ በሚገኘዉ የኔዘርላንድስ ፍርድ ቤት ተፈጽመዋል የተባሉ ዝርዝር በደሎችን ዛሬም የተደመጡ ሲሆን፤ አቃቤ ሕግም በቅጣት ሃሳቡ የዕድሜ ልክ እስራት ጠይቋል። ፍርድ ቤቱ የመቶ አለቃ እሸቱ ዓለሙን ጉዳይ ለፊታችን ሰኞ የቀጠረ ሲሆን የተከሳሹ ጠበቆች መከራከሪያቸዉን ያቀርባሉ ተብሎ ይጠበቃል። ዘሄይግ በሚገኘዉ ፍርድ ቤት የዛሬዉን ችሎት የተከታተሉ እና ኔዘርላንድስ ዉስጥ ከ35 ዓመታት በላይ የኖሩትን አቶ ሲራክ አስፋዉን የተከናወኑን እንዲያስረዱን በስልክ አነጋግሬያቸዋለሁ።

ሸዋዬ ለገሠ

ነጋሽ መሐመድ