1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዕርቅ እና ሰላም ኮሚሽን አደረጃጀት

ሐሙስ፣ ግንቦት 15 2011

የኢትዮጵያ መንግሥት ባለፉት ዓመታት የተፈጸሙ የመብት ጥሰቶችን እና በደሎችን በማጣራት ዕርቅ የሚያወርድ ሰላም የሚያሰፍን የብሔራዊ ዕርቀ ሰላም ኮሚሽን እና የአስተዳደር እና የማንነት ጥያቄዎችንም የሚያጣራ ኮሚሽን ማቋቋሙ ይታወሳል።

https://p.dw.com/p/3IyeP
20.06.2013 DW Online Karten Basis Aethiopien spanisch

የሕግ ባለሙያው ማብራሪያ

በተለይ የብሔራዊ ዕርቀ ሰላም ኮሚሽኑ የሚኖረውን ሚና እና ኃላፊነት ከመቋቋሚያ አዋጁ በመነሳት ያልተመለሱ ጥያቄዎች መኖራቸውን ያመለከቱት ዶይቼ ቬለ DW በጉዳዩ ላይ ያነጋገራቸው ከፍተና የሕግ ባለሙያ፤ በማኅበረሰቡ ውስጥ ሰላምና እርቅን ከማስፈን በዘለለ የሰብዓዊ መብቶች ጥሰትን ከመዳኘት አኳያ የተባለ ነገር አለመኖሩን አንስተዋል።  የብራስልሱ ዘጋቢያችን ገበያው ንጉሤ በጉዳዩ ላይ ያነጋገራቸው የሕግ ባለሙያው ዶክተር ዳዲሞስ ኃይሌ በብሪታንያው የብሪስቶል ዩኒቨርሲቲ ከፍተኛ ተመራማሪ እና በባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ደግሞ የሕግ ተባባሪ ፕሮፌሰር ናቸው። ከሰሞኑ ወደ ብራስልስ ብቅ  ባሉበት አጋጣሚ ገበያው በኮሚሽኑ አደረጃጀት ላይ አነጋግሯቸው ተከታዩን ዘገባ ልኮልናል።

ገበያው ንጉሤ

ሸዋዬ ለገሠ

ተስፋለም ወልደየስ