1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓፋር ክልል ችግረኞች

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 14 2014

በዓፋር ክልል በሰሜን ኢትዮጵያ  ለአንድ ዓመት በዘለቀው ጦርነት ምክንያት ወደ 376 ሺ የክልሉ ተወላጆች አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው አንድ የከልሉ ባለስልጣን አስታወቁ።

https://p.dw.com/p/44mGU
Karte Äthiopien Region Tigray DE

በሰሜን ኢትዮጵያ የአስቸኳይ እርዳታ ፈላጊው ቁጥር ወደ ሁለት ሚሊዮን ተጠግቷል

በዓፋር ክልል በተደረገዉ ጦርነት ምክንያት ወደ 376 ሺ የክልሉ ተወላጆች አስቸኳይ እርዳታ እንደሚያስፈልጋቸው አንድ የከልሉ ባለስልጣን አስታወቁ።
የዓፋር ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባብሪያ ጽሀፈት ቤት ሃላፊ አቶ መሃመድ ሁሴን ለዶቼቬለ እንደተናገሩት በተለይ በሰሜኑ የሃገሪቱ ክፍል በተፈጠረው ጦርነት የተፈናቀሉትን ጨምሮ  1.3 ሚልዮን ነዋሪዎች ለተለያዩ ችግሮች ተጋልጠዋል።
በሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ለአንድ ዓመት በዘለቀው ጦርነትና ከዒሳ ጎሳ በየጊዝው በሚፈጠሩ ግጭቶች ምክንያት  በክልሉ ተፈናቅለው በ12 የመጠለያ ጣብያዎቸ የሚገኙት ተፈናቃዮች ክልሉና የፌደራል መንግስት አስፈላጊውን እርዳታ ለማቅረብ ጥረት ቢያደርጉም በቂ እንዳይደለና አስቸኳይ እርዳታ እንድሚያስፈልጋቸው የዓፋር ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ማስተባብሪያ ጽሕፈት ቤት ሃላፊ አቶ መሃመድ ሁሴን ተናግረዋል።
የፌደራል አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን በበኩሉ ለአፋር ተፈናቃዮች ከ70ሺ 500 ኩንታል በላይ ምግብ ማከፋፈሉን አፍታውቋል።
ዮሃንስ ገብረእግዚአብሄር

ታምራት ዲንሳ

ኂሩት መለሰ