1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም የስደተኞች ቀን

ረቡዕ፣ ሰኔ 12 2011

በመላው ዓለም 71 ሚሊየን ሕዝብ በጦርነት፣ በክስ እና በሌሎች ጥቃቶች ምክንያት የሚኖሩበትን ስፍራ ጥለው ለመሰደድ  መገደዳቸውን የተመድ ዛሬ አመለከተ። ነገ የሚታሰበውን የዓለም የስደተኞች ቀን አስመልክቶ ዛሬ የወጣው ዘገባ እንደሚለው ይህ ቁጥር ከባለፈው ዓመት በ2 ሚሊየን ጨምሮ መታየቱንም ገልጿል።

https://p.dw.com/p/3Kich
Äthiopien Assosa | Teodoro Obiang Nguema Präsident von Equatorial Guinea Besucht Flüchtlingscam Tsore
ምስል DW/G. Tedla

«በነገው ዕለት በመላው ዓለም ይታሰባል»

ከተጠቀሰው ቁጥር 41 ሚሊየን የሚሆኑት ደግሞ በገዛ ሀገራቸው ውስጥ ከመኖሪያ ቀየው የተፈናቀሉ መሆናቸውን ዘገባው ይፋ አድርጓል። አፍሪቃ ውስጥ የስደተኞች እና የተፈናቃዮች ቁጥር እየጨመረ በመምጣቱ ለተፈናቃዮች፣ ለስደተኞች እና ከስደት ለሚመለሱት በቂ  ትኩረት እንዲሰጥ ጥረት እየተደረገ መሆኑ ተነግሯል። ይህን ለማስተባበር የአፍሪቃ ሕብረት የስደተኞች ጠበቃ እንዲሆኑ የተመረጡት የኢኳቶሪያል ጊኒ ፕሬዝደንት ኢትዮጵያ ውስጥ በአሶሳ ጾሬ የሚገኘውን ስደተኞች የሚኖሩበትን መጠለያ ስፍራ ጎብኝተዋል። በጉብኝቱ ወቅት በስፍራው የተገኘው ዘጋቢያችን ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ ዘገባ ልኮልናል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

ተስፋለም ወልደየስ