1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም ዜና

Azeb Tadesse ሐሙስ፣ ኅዳር 8 2009

https://p.dw.com/p/2Sr4o

 

የዓለም የምግብና እርሻ ድርጅት «FAO» ኢትዮጵያ ዘንድሮም በሌላ  ድርቅ ልትመታ እንደምትችል ባወጣዉ መግለጫ አስጠነቀቀ። የዝናቡ መቅረት ጉዳት  እያደረሰ መሆኑንና እንስሶት መሞታቸዉን የደቡብ ምይራብ ኢትዮጵያ ነዋሪዎች ለዶይቼ ቬለ ተናግረዋል። 

ጀርመንን በመጎብኘት ላይ የሚገኙት ተሰናባቹ የዩኤስ አሜሪካ ፕሬዚዳንት ባራክ ኦባማ የጀርመንዋንን  መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርክልን ጥብቅ ወዳጅና  በዓለም አቀፉ ፖለቲካ ጠንካራ አጋር  ሲሉ አወደሱ።

ሱዳን ሩስያ ከዓለም አቀፉ የጦር ወንጀለኞች መዳኛ ፍርድቤት መዉጣትዋን አወደሰች። «ICC» በዳርፉር ለተካሄደ  ጭፍጨፋ ፕሬዚዳንት ኦማር ኧል-ባሽርን ተጠያቂ በማድረግ  የእስር ማዘዣ እንደቆረጠላቸዉ ይታወቃል።