1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዓለም ባንክ ለታዳጊ ሃገራት የ12 ቢልዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ አጸደቀ።

ረቡዕ፣ ጥቅምት 4 2013

የዓለም ባንክ ታዳጊ ሃገራት የኮሮና ወረርኝን መከላከል የሚያስችላቸው የ12 ቢልዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ አጸደቀ። የገንዘብ ድጋፉ የኮሮና መከላከያ ክትባትን ጨምሮ ተህዋሲውን ለመመርመር እና የህክምና ዕርዳታ ለመስጠት የሚውል ሲሆን አንድ ቢልዮን ሰዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል።

https://p.dw.com/p/3jvfb
USA Wirtschaft Washington DC Zentrale der Weltbank Gebäude Logo
ምስል ullstein bild - Fotoagentur imo

የዓለም ባንክ ታዳጊ ሃገራት የኮሮና ወረርኝን መከላከል የሚያስችላቸው የ12 ቢልዮን ዶላር የገንዘብ ድጋፍ አጸደቀ። የገንዘብ ድጋፉ የኮሮና መከላከያ ክትባትን ጨምሮ ተህዋሲውን ለመመርመር እና የህክምና ዕርዳታ ለመስጠት የሚውል ሲሆን አንድ ቢልዮን ሰዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ ያለመ ነው ተብሏል። ባንኩ ትናንት አመሻሹ ላይ ባወጣው መግለጫ እንዳለው የገንዘብ ድጋፉ ባንኩ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል እና ተያይዘው የሚመጡ የአሰቸኳይ ጊዜ አደጋዎችን ለመቋቋም የያዘው የ160 ቢልዮን የገንዘብ ድጋፍ አካል ነው። በመርሃ ግብሩ 111 ሃገራት በባንኩ የአስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ፕሮግራም ተጠቃሚ መሆን መጀመራቸውንም ባንኩ አስታውቋል። አያይዞም በማደግ ላይ ባሉ ሃገራት የሚገኙ ዜጎች ደህንነቱ እና ፈዋሽነቱ የተረጋገጠ የኮቪድ 19 ክትባት ማግኘት እንዳለባቸው ባንኩ እምነቱ መሆኑን ገልጿል። እነዚህ ሃገራት ውጤታማ ክትባቶችን እንዲያገኙ እና በቂ አቅርቦት እንዲኖር ማስቻል እንዲሁም ከገቡበት ምጣኔ ሃብታዊ ችግር እንዲወጡ ተገቢው ድጋፍ እንዲደርሳቸው በማድረግ ላይ መሆናቸውን የባንኩ ፕሬዝዳንት ዴቪድ ማልፓስ ገልጸዋል። በተጨማሪም የዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት እና የግሉ ዘርፍ በዓለም ባንክ በኩል የኮሮና ክትባት ለሚያዘጋጁ 4 ቢልዮን ዶላር ሥራ ላይ መዋሉንም ፕሬዚዳንቱ ተናግረዋል። በአሁኑ ወቅት ተመራማሪዎች ከ170 በላይ የኮቪድ 19 መከላከያ ክትባትን በማበልጸግ ላይ መሆናቸውንም ባንኩ አስታውቋል።     
ታምራት ዲንሳ

ሸዋዬ ለገሠ