1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዒድ አከባበር በአዲስ አበባ እና የተከሰተዉ ኹከት

ሰኞ፣ ሚያዝያ 24 2014

1443 ኛውን የዒድ አልፈጥር በዓል በአዲስ አበባ ከተማ በድምቀት ተከብሮአል። ይሁንና በከተማዋ ስቴድዮም አካባቢ ለማክበር አደባባይ ከወጡ ምዕመናን እና የፀጥታ ፖሊሶች መካከል አነስተኛ ግጭት ተቀስቅሶ ፖሊስ አስለቃሽ ጢስ መጠቀሙን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቦአል።

https://p.dw.com/p/4Ajur
Äthiopien Schäden durch Auseinandersetzungen in Adis Abeba nach Beendigung des Ramadan
ምስል Seyoum Getu/DW

ፖሊስ አስለቃሽ ጢስ ተኩሶአል

ዛሬ 1443ኛውን የዒድ አልፈጥር በዓል በአዲስ አበባ ከተማ በድምቀት ተከብሮአል። ይሁንና በከተማዋ ስቴድዮም አካባቢ ለማክበር አደባባይ ከወጡ ምዕመናን እና የፀጥታ ፖሊሶች መካከል አነስተኛ ግጭት ተቀስቅሶ ፖሊስ አስለቃሽ ጢስ መጠቀሙን የፈረንሳይ ዜና አገልግሎት አዣንስ ፍራንስ ፕሬስ ዘግቦአል። አንድ  የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት አባል ለዜና ፈረንሳይ የዜና አገልግሎት እንደገለፁት ፖሊስ አስለቃሽ ጢስ የተጠቀመበት ምክንያት ግልፅ አይደለም።  ከአዲስ አበባ በደረሰን መረጃ መሰረት መስቀል አደባባይ አካባቢ የሚገኙ ሕንፃ መስኮቶች ተሰባብረዋል። አንድ ቡና ቤት ያለ ቁሳቁስ ወድሞአል። የአደባባይ አትክልቶች ተነቃቅለዋል። ይህን ቃለ መጠይቅ አዲስ አበባ ከሚገኘዉ ወኪላችን ጋር ካደረግን በኋላ ፖሊስ መግለጫ ለመስጠት እየተዘጋጀ መሆኑን አዲስ አበባ የሚገኘዉ ስዩም ጌቱ ያደረሰን መረጃ ያመለክታል።

 

ስዩም ጌቱ

አዜብ ታደሰ

እሸቴ በቀለ