1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

  የዐባይ ግድብና የሱዳን ቀዉስ

ማክሰኞ፣ ሚያዝያ 15 2011

ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ ሥለ ግድቡ ግንባታ በቅርቡ ሊያደርጉት የነበረዉ ዉይይት ለሌላ ጊዜ ተራዝሟል። የሚንስቴሩ ባለሥልጣናት ዛሬ እንዳሉት ግን አዲሶቹ የሱዳን መሪዎች ሱዳን ሥለ ኢትዮጵያ የምታራምደዉ መርሕ እንደማይለወጥ ተናግረዋል።

https://p.dw.com/p/3HIOr
Äthiopien Grand Renaissance Staudamm
ምስል Reuters/T. Negeri

«የሱዳን ቀዉስ የባይን ግድብ አያጉልም» ኢትዮጵያ


የሱዳን ፖለቲካዊ ቀዉስ ኢትዮጵያ በአባይ ግድብ ላይ በምታስገነባዉ የኤሌክትሪክ ኃይል ማመንጫ ሥራ ላይ የሚያሳድረዉ ተፅዕኖ እንደሌለ የኢትዮጵያ የዉኃ፣ የመስኖና የኢነርጂ ሚንስቴር አስታወቀ። ኢትዮጵያ፣ ሱዳንና ግብፅ ሥለ ግድቡ ግንባታ በቅርቡ ሊያደርጉት የነበረዉ ዉይይት ለሌላ ጊዜ ተራዝሟል። የሚንስቴሩ ባለሥልጣናት ዛሬ እንዳሉት ግን አዲሶቹ የሱዳን መሪዎች ሱዳን ሥለ ኢትዮጵያ የምታራምደዉ መርሕ እንደማይለወጥ ተናግረዋል። ባለስልጣናቱ አክለዉ እንዳሉት በግድቡ ሥራ ይሳተፍ የነበረዉ የኢትዮጵያ መከላከያ ብረታብረትና ኢንጂነሪግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ይዞት የነበረዉ ሥራ በሌሎች እስኪተካ ድረስ የግድቡ ግንባታ ተጓትቷል።

ሰለሞን ሙጬ

ነጋሽ መሐመድ

ተስፋለም ወልደየስ