1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

ሐሙስ፣ ታኅሣሥ 4 2011

በተለያዩ ሃገራት ተሰድደው የጉዞ ሰነድ ሳይኖራቸው ሀገር አልባ ሆነው የቆዩ ዜጎች ፓስፖርት እንዲያገኙ እየተደረገ መሆኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታወቀ። ባለፉት ጥቂት ወራትም 40 ሺህ የሚሆኑ ዜጎች የጉዞ ሰነድ እንዲያገኙ መደረጉ ነው የተነገረው።

https://p.dw.com/p/3A3Vd
Äthiopien Meles Alem Sprecher Außenministerium
ምስል DW/G. Tedla

«ለ40 ሺህ ዜጎች የይለፍ ሰነድ ተሰጥቷል»

በሚኖሩበት ሀገር በወንጀል ተጠያቂ ለሆኑ ኢትዮጵያውያንም ዲፕሎማሲያዊ መፍትሄ እንደተገኘ ተገልጿል። በተለይ በሳውድ አረቢያ እስር ቤቶች የሚገኙ ዜጎች መንግሥት ባደረገው ድርድር የእስር ጊዜያቸውን ሳይጨርሱ ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ማስቻሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ መለስ ዓለም ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ዘርዝረዋል። መግለጫውን የተከታተለው የአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ዝርዝሩን ልኮልናል።

ጌታቸው ተድላ ኃይለ ጊዮርጊስ

ሸዋዬ ለገሠ

እሸቴ በቀለ