1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር መግለጫ

ሐሙስ፣ ሚያዝያ 13 2014

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የሕብረቱ የአፍሪቃ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ ተፋላሚ ኃይላትን ለመሸምገል የሚያደርጉትን ጥረት ኢትዮጵያ እንደምትደግፍ አስታዉቀዋል።

https://p.dw.com/p/4AFAp
Äthiopien l Sprecher des Außenministeriums - Dina Mufti
ምስል Solomon Muchie/DW

የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር የአፍሪቃ ሕብረትን አወደሰ

         

የአፍሪካ ሕብረት ኢትዮጵያን በተመለከተ እስካሁን የተከተለውን መርሕ የኢትዮጵያ  ዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር "ገንቢ" በማለት አወደሰዉ።የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ዐቀባይ ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የሕብረቱ የአፍሪቃ ቀንድ ልዩ መልእክተኛ ተፋላሚ ኃይላትን ለመሸምገል የሚያደርጉትን ጥረት ኢትዮጵያ እንደምትደግፍ አስታዉቀዋል።አምባሳደር ዲና እንዳሉት የኢትዮጵያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን የመንግስታቸዉን አድናቆትና ድጋፍ ለሕብረቱ የሰላምና የፀጥታ የበላይ ኃላፊ ገልፀዋል።

ሰሎሞን ሙጬ 

ነጋሽ መሐመድ

እሸቴ በቀለ