የዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር መግለጫ
ሐሙስ፣ ነሐሴ 27 2013ማስታወቂያ
የኢትዮጵያ መንግስት በየሐገሩ የሚገኙ የኤምባሲ ፅሕፈት ቤቶችን ሲዘጋ የተወሰኑ ዲፕሎማቶች በየነበሩበት ሐገራት ጥገኝነት መጠየቃቸዉን የዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር አረጋገጠ።የዉጪ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ዛሬ በሰጡት መግለጫ የዲፕሎማቶቹን ዉሳኔ «አሳፋሪ» ብለዉታል።አምባሳደር ዲና ዛሬ ኢትዮጵያን ስለጎበኙት ስለኬንያ ዉጪ ጉዳይ ሚንስትር ተልዕኮ፣ሰሜን ኢትዮጵያ ዉስጥ ስለሚደረገዉ ዉጊያ እና ስለርዳታ አቅርቦቱ ከጋዜጠኞች ለቀረበላቸዉ ጥያቄ መልስና ማብራሪያ ሰጥተዋል።
ሰለሞን ሙጬ
ነጋሽ መሐመድ
ኂሩት መለሰ