1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የወጣቶች ግጭት በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ቡልቡላ ወረዳ

ማክሰኞ፣ ጥቅምት 11 2012

ሰኞ መስከረም 10/ 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ቡልቡላ ወረዳ 12 ከረፋዱ 3 ሰዓት ጀምሮ በተፈጠረ የወጣቶች ግጭት የተወሰኑት ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል ሲገቡ እስከ ሁለት መቶ የሚደርሱት ታስረዋል።

https://p.dw.com/p/3RjGz
Blick aus meinem Fenster Addis Abeba Äthiopien
ምስል Solomon Mengist

አረንጓዴ፣ቢጫ፣ ቀይ ቀለምና ከጀርባው የምኒልክ ምስል ያለዉ ቲሸርት "ለምን ለበስሽ? በሚል ነዉ

ሰኞ መስከረም 10/ 2012 ዓ.ም በአዲስ አበባ ቦሌ ክፍለ ከተማ ቡልቡላ ወረዳ 12 ከረፋዱ 3 ሰዓት ጀምሮ በተፈጠረ የወጣቶች ግጭት የተወሰኑት ጉዳት ደርሶባቸው ሆስፒታል ሲገቡ እስከ ሁለት መቶ የሚደርሱት ለእስር መዳረጋቸውን ዶቼ ቬለ / DW /ያነጋገራቸው የአካባቢ ነዋሪዎች ተናገሩ። ግጭቱ የተቀሰቀሰው አረንጓዴ ፣ ቢጫ ፣ ቀይ ቀለም ያለውና ከጀርባው የምኒልክ ምስል የታተመበትን ቲሸርት "ለምን ለበስሽ? " ፤ " ብለብስስ  " በሚል የተጀመረ ነው ያሉት የአይን እማኞች ሁኔታው ከአካባቢው ፖሊስ አቅም በላይ ሆኖ በርከት ያሉ የፌዴራል ፖሊስ አባላት ከደረሱ በኋላ ሊበርድ መቻሉንም ተናግረዋል። ክስተቱን ተከትሎ ወደ 2 መቶ የሚደርሱ ወጣቶች ታስረው እንደነበርና አብዛኞቹ ቢፈቱም ወደ 50 ያህሉ አሁንም አለመፈታታቸውንም አስታውቀዋል። ችግረል በተከሰትልበት ክፍለ ከተማና የአካባቢው የማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ አገልግሎት ጣቢያ ተገኝተን እንደተመለከትነው ፣ ወጣቶች ታስረዋል ጠያቂዎችም ያለ እረፍት ወደ ጣቢያው ሲገቡና ሲወጡ ተመልክተናል። ጥፋቱን አደረሱ የተባሉትን ወጣቶች እንዲሁም የከተማዋን ፖሊስ ስለ ጉዳዩ ተጨማሪ ማብራሪያዎችን ለማግኘት ጥረት ብናደርግም ሊሳካ አልቻለም ።

ሰለሞን ሙጬ 

አዜብ ታደሰ 

ተስፋለም ወልደየስ