1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኮንትሮባንድ ሲጋራና መዘዙ

ረቡዕ፣ ሰኔ 29 2014

በዓለም ላይ ከሚሸጡ ዐሥር ሲጋራዎች አንዱ በሕገወጥ መንገድ የሚሸጥ ነው፡፡ በኛ ሐገር ግን በመንግስት ቁጥጥር የሚመረቱና ወደ ሃገርቤት የሚገቡ የሲጋራ ዓይነቶች 6 ቢሆኑም በአገሪቱ ውስጥ ወደ 80 የሚሆኑ ስጋራዎች በሕገወጥ መንገድ ገብተው በግላጭ ይቸበቸባሉ።

https://p.dw.com/p/4Dk7R
Flash-Galerie Rauchen und Gesundheit
ምስል AP

የኮንትሮባንድ ሲጋራዎችና መዘዛቸው

ወደ ኢትዮጵያ በሕገወጥ መንገድ ወይንም በኮንትሮባንድ የሚገቡ ሲጋራዎች ለተለያዩ የካንሰር በሽታዎች ሊያጋልጡ ስለሚችሉ ጥንቃቄ እንደሚያስፈልግ የጤና ባለሞያዎች አስጠነቀቁ።
በአገሪቱ ገበያ ላይ ከሚዘዋወሩ ሲጋራዎች 63 በመቶ ገደማ በኮንትሮባንድ የገቡና ተገቢውን መስፈርት የማያሟሉ እንደሆኑ ጥናቶች ያመላክታሉ።
‹‹እኛ ሞራል ኖሮን ስለ ጤና ማውራት ባንችልም  በሕገወጥ መንገድ የሚገቡ የሲጋራ ምርቶች በጤና ላይ ጉዳት እያስከተሉ ነው›› ሕገወጥ ንግድ በተለያዩ ዘርፎች እያስከተለ ያለውን ከፍተኛ ጉዳት በተመለከተ በአዲስ አበባ ንግድና ዘርፍ ማኅበራት ምክር ቤት በተዘጋጀ የውይይት መድረክ ላይ ተገኝተው ማብራሪያ የሰጡት የጃፓን ቶባኮ ኢንተርናሽናል ተወካይ ከተናገሩት የተወሰደ። እኛም በዚህ የኮንትሮባንድ ስርጭት መንግስት በየዓመቱ ስለሚከስረው በቢልዮን የሚቆጠር ብር ሳይሆን ሲጋራ የዜና ጠንቅነቱን የባለሙያ ምልከታ ፍለጋ ሁለት ሀኪሞችን አነጋግረናል።

 ህገወጥ የሲጋራ ምርቶች የሀገሪቱን ገበያ 63 በመቶ ገደማ  የተቆጣጠረውት ይገኛሉ።  በኮንትሮባንድ የሚገባ ደረጃውን ያልጠበቀ ሲጋራ በሕዝብ ጤና ላይ የሚኖረው ጉዳት እንዲያጋሩን የጤና ባለሞያዋ ዶክተር ቤዛዊት ወልደአረጋይ ``በተለይ በልብና ደምስሮች ላይ ከፍተኛ ችግር ያስከትላል። የተለያዩ የሳንባ ህመሞች ያስከትላል። ከምንም በላይ ግን ለሁሉም ዓይንት የካንሰር ህመሞች ጠንቅነው። እርጉዝሴቶች በሚያጨሱበት ጊዜ በጽንሱ ላይና በልጁ ቀጣይ ህይወት ከፍተኛ ጉዳት ያደርሳል። ሁሉም ሲጋራዎች ባናጨስ ይመከራል በተለይም በኮንትሮባንድ የሚገቡትን ደግሞ ልዩ ጥንቃቄ ያስፈልጋል`` ብሏል።

በዓለም ላይ ከሚሸጡ ዐሥር ሲጋራዎች አንዱ በሕገወጥ መንገድ የሚሸጥ ነው፡፡ በኛ ሐገር ግን በመንግስት ቁጥጥር የሚመረቱና ወደ ሃገርቤት የሚገቡ የሲጋራ ዓይነቶች 6 ቢሆኑም በአገሪቱ ውስጥ ወደ 80 የሚሆኑ ስጋራዎች በሕገወጥ መንገድ ገብተው በግላጭ ይቸበቸባሉ። እነዚህ ሲጋራዎች ቁጥጥር ስለማይደረግባቸው ዓለምአቀፍ መስፈርት እንደማያሟሉ ይህም ካንሰርን ጨምሮ ለተለያዩ የጤና እክሎች እንደሚዳርግ ጠቅላላ ሐኪም ግርማ ለገሰ ነግረውናል። ብዙ አጫሾች ማጨስን ለማቆም ሲቸገሩ ይስተዋላል። ዶክተር ቤዛዊት ግን ማቆም ቢከብድም በሕክምና ተደግፎ ማቆም ይቻለል ሲሉ ይመክራሉ።
 በሕገወጥ መንገድ ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡት የሲጋራ ምርቶች የሚመጡት ከዩናይትድ ዓረብ ኤምሬትስ፣ ከየመንና ከኬንያ ሲሆን ወደ ኢትዮጵያ የሚገቡት ደግሞ በሶማሌ ላንድና በጂቡቲ ድንበር በኩል መሆኑ ታውቋል።

Abbildung Abhängigkeit
ምስል Fotolia/Marina

ዮሐንስ ገብረእግዚአብሄር።

ማንተጋፍቶት ስለሺ