1. ወደ ይዘቱ ዝለል
  2. ወደ ዋናዉ ገፅ ዝለል
  3. ወደ ተጨማሪ የDW ድረ-ገፅ ዝለል

የኮሮና ወቅታዊ ኹኔታ በኢትዮጵያ

ማክሰኞ፣ ግንቦት 2 2014

ሰሞኑን በኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል በኮሮና ተሐዋሲ ተጠቅቶ ይታከም የነበረ የመጨረሻው ታካሚ ወደ ቤቱ መሸኘቱ ተሰምቷል። ይህ ማለት ግን ኮሮና ከኢትዮጵያ ተወገደ ማለት አይደለም ይላሉ ባለሞያዎች። ወደ ሐኪም ቤቱ የሚመጡ ሰዎች ቁጥር እጅግ ቢቀንስም ማኅበረሰቡ አሁንም ጥንቃቄ እንዲያደርክግ የጤና ባለሞያዎች ይመክራሉ።

https://p.dw.com/p/4B68y
Äthiopien | Eka Kotebe General Hospital
ምስል Hanna Demissie/DW

ማኅበረሰቡ አሁንም ጥንቃቄ እንዲያደርግ ተብሏል

ሰሞኑን በኤካ ኮተቤ አጠቃላይ ሆስፒታል በኮሮና ተሐዋሲ ተጠቅቶ ይታከም የነበረ የመጨረሻው ታካሚ ወደ ቤቱ መሸኘቱ ተሰምቷል። ይህ ማለት ግን ኮሮና ከኢትዮጵያ ተወገደ ማለት አይደለም ይላሉ ባለሞያዎች። ወደ ሐኪም ቤቱ የሚመጡ ሰዎች ቁጥር እጅግ ቢቀንስም ማኅበረሰቡ አሁንም ጥንቃቄ እንዲያደርግ የጤና ባለሞያዎች ይመክራሉ። 

ኮሮና ተሐዋሲ ኮቪድ 19 በ እንደጎርጎሮሳውያኑ አቆጣጠር በ2019 በቻይና ዉሀን በተሰኝችው ከተማ መከሰቱ ከተሰማበት ግዜ ጀምሮ ያላዳረሰው የዓለማችን ክፍል የለም ማለት ይቻላል። ይህ ከዚያን ጊዜ በፊት በሰዎች ውስጥ ተገኝቶ የማያውቀው ተሐዋሲ የዓለምን ማኅበረሰብ ከሊቅ እስከደቂቅ የተለመደ የለት ተእለት የአንዋንዋር ዘይቤ መልክ እንዲቀይር አስገድዶዋ። የዓለምን የምጣኔሀብትም ማሽመድመዱ ይታወሳል በሀገራችን ም ላለፉት ሁለት አመታት የኮቪድ 19 ማእካል ሆኖ ሲያገለግል የቆየው ኤካ ኮተቤ ሆስፒታል ባለፈው ሳምት ሆስፒታሉ በሁለት አመት ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ያለ ኮቪድ19 ታካሚ ውሎ ማደሩን ስራ አስኪያጁ ዶ/ር ያሬድ አግደው ገልፀዋል። የፅኑ ህሙማን ቁጥር ከግዜ ወደግዜ እየቀነሰ ቢመጣም ኅብረተሰቡ ጥንቃቂ እንዲያደርግ ነው ያነጋገርናቸው ባለሙያዎች ያሳስባሉ። 

ሐና ደምሴ

ማንተጋፍቶት ስለሺ