የኮሮና ተሐዋሲ ስርጭት በኦሮሚያ ክልል
ዓርብ፣ መጋቢት 10 2013ማስታወቂያ
በኦሮሚ ክልል መጠኑ ከፍ ማለት የጀመረው የኮሮና ተሐዋሲ ስርጭት ከፍተኛ ስጋት መደቀኑን የክልሉ ጤና ጽ/ቤት ዐስታወቀ። በጤና ጽ/ቤቱ የኅብረተሰብ ጤና ድንገተኛ ቁጥጥር ዘርፍ ኃላፊ ለዶይቼ ቬለ (DW) እንደገለጹት፤ የቅርብ አሃዞች የሚያመለክቱት የኮሮና ተሐዋሲ ስርጭት ብቻ ሳይሆን በተሐዋሲው የተነሳሱ ሕይወታቸውን የሚያጡ ሰዎችም ቊጥር እየጨመረ ነው። በተለይም ባለፉት ሰባት ቀናት በክልሉ በየቀኑ የሚመዘገበው የበሽታው የስርጭት መጠን ከግማሽ በመቶ ከፍ ማለቱን የክልሉ ጤና ጽ/ቤት አክሎ አብራርቷል። ሥዩም ጌቱ ዝርዝር ዘገባ ልኮልናል።
ሥዩም ጌቱ
ማንተጋፍቶት ስለሺ
እሸቴ በቀለ